Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 26:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በፈረሶቹ ኮቴዎች ጎዳናዎችሽን ሁሉ ይረጋግጣል፥ ሕዝብሽንም በሰይፍ ይገድላል፥ የብርታትሽ ምሰሶዎች ወደ መሬት ይወድቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 መንገዶችሽ ሁሉ በፈረሶቹ ኰቴ ይረጋገጣሉ፤ ሕዝብሽን በሰይፍ ይገድላል፤ ታላላቅ ምሰሶዎችሽ ወደ ምድር ይወድቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ሠራዊቱ በፈረሶቹ ሰኰናዎች መንገዶችሽን ይረጋግጣል፤ ሕዝብሽን በሰይፍ ይገድላል፤ ጠንካራ ዐምዶችሽም ወደ መሬት ይወድቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ፈረ​ሶቹ አደ​ባ​ባ​ይ​ሽን ይረ​ግ​ጣሉ፤ ሠራ​ዊ​ቶ​ች​ሽ​ንም በሾ​ተል ይገ​ድ​ሏ​ቸ​ዋል፤ የጸና አር​በ​ኛ​ሽ​ንም በም​ድር ላይ ይጥ​ለ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በፈረሶቹ ኮቴ ጎዳናዎችሽን ሁሉ ይረመርማል፥ ሕዝብሽንም በሰይፍ ይገድላል፥ የብርታትሽም ሐውልት ወደ ምድር ይወድቃል።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 26:11
5 Referencias Cruzadas  

በከፍታ የሚኖሩትን ሰዎች ዝቅ ያደርጋል፤ ከፍ ያለችውን ከተማ ያዋርዳል፥ እስከ መሬትም ድረስ ያወርዳታል፥ እስከ ትቢያም ድረስ ይጥላታል።


ፍላጻቸው የተሳለ፤ ቀስታቸውም የተደገነ ነው፤ የሠረገሎቻቸውም መንኮራኩሮች እንደ ዐውሎ ነፋስ ናቸው።


በግብጽም ምድር ያለውን የሄልዮቱን ከተማ ሐውልቶች ይሰብራል፥ የግብጽንም አማልክት ቤቶች በእሳት ያቃጥላል።’ ”


በምድር ላይ ዓላማን አንሡ በአሕዛብም መካከል መለከት ንፉ፥ አሕዛብንም ለጦርነት በእርሷ ላይ አዘጋጁ፤ የአራራትንና የሚኒን የአስከናዝንም መንግሥታት ጥሩባት አለቃንም በእርሷ ላይ ሹሙ፤ እንደ ጠጉራም ኩብኩባ ፈረሶችን በእርሷ ላይ አውጡ።


ፈረሶቻቸው ከነብር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው፥ ከማታም ተኩላ ይልቅ አስፈሪዎች ናቸው፤ ፈረሰኞቻቸውም ይንሳፈፋሉ፥ ፈረሰኞቻቸው ከሩቅ ይመጣሉ፥ ለመንጠቅ እንደሚቸኩል ንስር ይበርራሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos