Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 23:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 በዓይኗም ባየቻቸው ጊዜ በፍትወት ተከተለቻቸው፥ ወደ ከላውዴዎን ምድር ወደ እነርሱ መልእክተኞችን ላከች።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ባየቻቸውም ጊዜ በፍትወት ተቃጠለች፤ ወደ ከላውዴዎን መልእክተኞች ላከችባቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ልክ እነርሱን ስታይ በፍትወት ተቃጥላ እነርሱ ወደሚኖሩባት ወደ ባቢሎን መልእክተኞችን ላከች፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ዐይ​ን​ዋ​ንም ወደ እነ​ርሱ አቅ​ንታ አየ​ቻ​ቸው፤ ወደ ከላ​ው​ዴ​ዎ​ንም ምድር ወደ እነ​ርሱ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ባየቻቸውም ጊዜ በፍቅር ተከተለቻቸው፥ ወደ ከላውዴዎን ምድር ወደ እነርሱ መልእክተኞችን ላከች።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 23:16
17 Referencias Cruzadas  

በከነዓን ምድር ከከላውዴዎን ጋር አመንዝራነትሽን አበዛሽ። በዚህም አልረካሽም።


እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ወደ ሴት አይቶ የተመኛት ሁሉ ከወዲሁ በልቡ ከእርሷ ጋር አመንዝሮአል።


ምንዝር የሞላባቸው ኃጢአትንም የማይተዉ ዐይኖች አላቸው፤ የማይጸኑትን ነፍሳት ያታልላሉ፤ መመኘትን የለመደ ልብ አላቸው፤ የተረገሙ ናቸው።


የሰጠሁሽን ከወርቄና ከብሬ የተሠራውን የሚያምር ጌጣጌጥ ወስደሽ የወንድ ምስሎች ለራስሽ ሠራሽ፥ ከእነርሱም ጋር አመነዘርሽ።


ዐይኖችህ ልዩ ነገሮችን ያያሉ፥ ልብህም ጠማማ ነገርን ይናገራል።


ውበትዋን በልብህ አትመኘው፥ በዐይኖችዋም አትማረክ።


ከንቱ ነገርን እንዳያዩ ዐይኖቼን መልስ፥ በመንገድህ ሕያው አድርገኝ።


“ከዐይኖቼ ጋር ቃል ኪዳን ገብቻለሁ፥ እንግዲህ ቈንጆይቱን እንዴት በፍትወት እመለከታለሁ?


ኢዮአቄም በነገሠ ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ይሁዳን ወረረ፤ ኢዮአቄምም ሦስት ዓመት ከገበረለት በኋላ እንደገና ዐመፀ፤


አንድ ቀን ማታ፥ ዳዊት ከአልጋው ተነሥቶ በቤተ መንግሥቱ ሰገነት ወዲያና ወዲህ ይመላለስ ነበር፤ ከሰገነቱ ላይ እንዳለም፥ አንዲት ሴት ገላዋን ስትታጠብ አየ፤ ሴቲቱም እጅግ ውብ ነበረች።


እያደርም የጌታው ሚስት ዐይኗን ጣለችበት፤ አፍ አውጥታም፥ “አብረኸኝ ተኛ” አለችው።


የእግዚአብሔር ልጆችም የሰውን ሴቶች ልጆች መልካሞች እንደ ሆኑ አዩ፥ ከመረጡአቸውም ሁሉ ሚስቶችን ለራሳቸው ወሰዱ።


ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደሆነ፥ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፥ ጥበብ ለማግኘትም የሚመኙት እንደሆነ አየች፤ ከፍሬውም ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው፤ እርሱም በላ።


ዘይትም ይዘሽ ወደ ንጉሡ ሄድሽ፥ ሽቱሽንም አበዛሽ፥ መልእክተኞችሽንም ወደ ሩቅ ላክሽ፥ እስከ ሲኦልም ድረስ ተዋረድሽ።


በወገባቸው ዝናር የታጠቁ፥ በራሳቸውም ላይ መጠምጠሚያ ያንጠለጠሉ፥ ሁሉም የተወለዱባት አገር የከለዳ የሆነች የባቢሎን ልጆች የሆኑትን ባለሥልጣኖችን ይመስሉ ነበር።


ሥጋቸው እንደ አህዮች ሥጋ፥ ዘራቸውም እንደ ፈረሶች ዘር የሆነውን እነዚያን ምልምሎች በፍትወት ተከተለቻቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios