ሕዝቅኤል 21:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ኃጢአታችሁን ስለ አሰባችሁ መተላለፋችሁም ስለ ተገለጠ ኃጢአታችሁም በሥራችሁ ሁሉ ስለ ታየ እናንተም ስለ ታሰባችሁ፥ በእጅ ትያዛላችሁ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም24 “ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እናንተ በምታደርጉት ሁሉ ኀጢአታችሁን በመግለጽ፣ በግልጽም በማመፅ በደላችሁን ስላሳሰባችሁ፣ እንዲህም ስላደረጋችሁ በምርኮ ትወሰዳላችሁ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 እንግዲህ እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምለው ይህ ነው፤ ኃጢአታችሁ ተገልጦአል፤ በደለኞች መሆናችሁን ሰው ሁሉ ያውቃል፤ በምታደርጉት ነገር ሁሉ ኃጢአተኞች መሆናችሁን ታሳያላችሁ፤ ስለዚህ ተማርካችሁ ትሄዳላችሁ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 “ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ኀጢአታችሁን ስለ ዐሰባችሁ፥ መተላለፋችሁም ስለ ተገለጠ፥ ኀጢአታችሁም በሥራችሁ ሁሉ ስለ ታየ፥ እናንተም ስለ ታሰባችሁ፥ በእርሱ ትያዛላችሁ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ኃጢአታችሁን ስለ አሰባችሁ መተላለፋችሁም ስለ ተገለጠ ኃጢአታችሁም በሥራችሁ ሁሉ ስለ ታየ እናንተም ስለ ታሰባችሁ፥ በእጅ ትያዛላችሁ። Ver Capítulo |