Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 19:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ነገር ግን በቁጣ ተነቀለች፥ ወደ መሬትም ተጣለች፤ የምሥራቅ ነፋስ ፍሬዋን አደረቀ፤ ብርቱ ቅርንጫፎቿም ተሰበሩና ደረቁ፤ እሳትም በላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ነገር ግን በቍጣ ተነቀለች፤ ወደ ምድርም ተጣለች። የምሥራቅ ነፋስ አደረቃት፤ ፍሬዎቿንም አረገፈባት። ብርቱዎቹ ቅርንጫፎቿ ክው አሉ፤ እሳትም በላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ነገር ግን በቊጣ ከስሩ ተነቅሎ ወደ ምድር ተጣለ። ከበረሓ የሚነሣ የምሥራቅ ነፋስ አደረቀው፤ ፍሬዎቹም ረገፉ፤ ብርቱ የሆኑት ቅርንጫፎቹም ደረቁ፤ እሳትም በላቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ነገር ግን በመ​ዓት ተነ​ቀ​ለች፤ ወደ መሬ​ትም ተጣ​ለች፤ የሚ​ያ​ቃ​ጥ​ልም ነፋስ ፍሬ​ዋን አደ​ረቀ፤ ብር​ቱ​ዎች በት​ሮ​ች​ዋም ተሰ​በ​ሩና ደረቁ፤ እሳ​ትም በላ​ቻ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ነገር ግን በመዓት ተነቀለች ወደ መሬትም ተጣለች የምሥራቅም ነፋስ ፍሬዋን አደረቀ፥ ብርቱዎች በትሮችዋም ተሰበሩና ደረቁ፥ እሳትም በላቻቸው።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 19:12
32 Referencias Cruzadas  

በወንድሞቹ መካከል ፍሬያማ ቢሆንም እንኳ የምሥራቅ ነፋስ ይመጣል፥ የጌታ ነፋስ ከምድረበዳ ይመጣል፤ ፈሳሹንም ይጠፋል፥ ምንጩንም ይደርቃል፥ የተከበሩ ዕቃዎች ሁሉ ያሉበትን መዝገብ ይበዘብዛል።


እነሆ ሲተከልስ ያድግ ይሆንን? የምሥራቅ ነፋስ በመታው ጊዜ ፈጽሞ አይደርቅምን? በተተከለበት መደብ ላይ ይደርቃል።


ጫፎችዋ በደረቁ ጊዜ ይሰበራሉ፥ ሴቶችም መጥተው ያቃጥሉአቸዋል፤ የማያስተውል ሕዝብ ነውና ፈጣሪው አይራራለትም፤ ሠሪውም ምሕረት አያደርግለትም።


ገዢዎች ለሚይዙት በትረ መንግሥት የሚሆኑ ብርቱ ቅርንጫፎች ነበሩአት፤ ቁመቱ ከቅርንጫፎች መካከል ረዥም ነበር፥ በርዝመቱና በቅርንጫፎቹ ብዛት ታየ።


እነሆ ለመቃጠል ለእሳት ተስጥቷል፥ እሳቱም ሁለቱን ጫፎቹን በልቶታል፥ መካከሉም ተቃጥሏል፥ ለሥራ ይጠቅማልን?


እንዲህም ይሆናል፤ እነርሱን ልነቅላቸውና ልሰባብራቸው፥ ላፈርሳቸውና ላጠፋቸው፥ ክፉም ላደርግባቸው እንደ ተጋሁ፥ እንዲሁ ልሠራቸውና ልተክላቸው እተጋለሁ፥ ይላል ጌታ።


በእኔ የማይኖር ቢሆን እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጭ ይጣላል፤ ይደርቅማል፤ እነርሱንም ሰብስበው ወደ እሳት ይጥሉአቸዋል፤ ያቃጥሉአቸውማል።


አሁንም ምሳር በዛፎች ሥር ተቀምጦአል፤ እንግዲህ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል ወደ እሳትም ይጣላል።


በውበትህ ምክንያት ልብህ ኰርቶአል፤ ከክብርህ የተነሣ ጥበብህን አረከስህ፤ በምድር ላይ ጣልሁህ ያዩህም ዘንድ በነገሥታት ፊት ሰጠሁህ።


ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ከዚህ ሰው ዘር የሚከናወንለት የለም፥ በዳዊትም ዙፋን ላይ የሚቀመጥ በይሁዳም የሚነግሥ ከእንግዲህ ወዲህ አይገኝምና፦ መካን በዘመኑም የማይከናወንለት ሰው ብላችሁ ጻፉ።”


ቀኝህ እጅህ የተከለውን፥ ለራስህ ያጸናኸውን ልጅ ጠብቅ።


ከመልካም ይልቅ ክፋትን፥ ጽድቅንም ከመናገር ይልቅ ዓመፃን ወደድህ።


ኢዮአቄም ሞተ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ኢኮንያን ነገሠ።


ንጉሥ ኒካዑ የኢዮስያስ ልጅ ኤልያቄም በአባቱ በኢዮስያስ እግር ተተክቶ በይሁዳ እንዲነግሥ አደረገ፤ ስሙንም በመለወጥ ኢዮአቄም ብሎ ጠራው፤ ኢዮአሐዝም በንጉሥ ነኮ ተማርኮ ወደ ግብጽ ተወሰደ፤ በዚያም ሞተ።


በኢዮስያስ ዘመነ መንግሥት ነኮ የተባለው የግብጽ ንጉሥ የአሦርን ንጉሠ ነገሥት ለመርዳት ሠራዊቱን እየመራ ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ተጓዘ፤ ንጉሥ ኢዮስያስም መጊዶ ላይ የግብጽን ሠራዊት ለማገድ ጦርነት ገጥሞ በዚያ ውጊያ ላይ ተገደለ፤


እሳት ከቁጣዬ ትነድዳለች፤ እስከ ሲኦል ድረስ ታቃጥላለች፤ ምድርንም ከፍሬዋ ጋር ትበላለች፤ የተራሮችን መሠረትም ታነድዳለች።’”


በቁጣና በመቅሠፍት፥ በታላቅም መዓት ጌታ ከምድራቸው ነቀላቸው፤ ወደ ሌላም ምድር ጣላቸው። ዛሬም በዚያው ይገኛሉ።’


የምሥራቅ ነፋስ እንደሚነፍስበት ቀን በጠንካራ ዐውሎ አስወገዳቸው፤ በጦርነት ሰደዳቸው፥ ቀሰፋቸውም።


አሌፍ። ጌታ በቁጣው የጽዮንን ሴት ልጅ እንደምን አደመናት! የእስራኤልን ውበት ከሰማይ ወደ ምድር ጣለ፥ በቁጣውም ቀን የእግሩን መረገጫ አላሰበም።


ፀሐይም በወጣ ጊዜ እግዚአብሔር የሚያቃጥል የምሥራቅ ነፋስ አዘጋጀ፥ ዮናስ ራሱን እስኪስት ድረስ ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለነፍሱም ሞትን ለመነና “ከሕይወት ሞት ይሻላል” አለ።


የሰው ልጅ ሆይ፥ በዱር ዛፎች መካከል ያለው የወይን ቅርንጫፍ፥ ከሁሉም ዛፎች ይልቅ የወይን ግንድ የሚበልጠው እንዴት ነው?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios