Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 18:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ጻድቁ ከጽድቁ ቢመለስ፥ በደልንም ቢሠራ፥ በዚያ ቢሞት፥ እርሱ በሠራው በደል ይሞታል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ጻድቅ ከጽድቁ ተመልሶ ክፉ ቢሠራ በክፋቱ ይሞታል፤ ከፈጸመውም በደል የተነሣ በሕይወት አይኖርም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ጻድቅ ሰው መልካም ማድረጉን ትቶ ክፉ ሥራ ሠርቶ ቢሞት የሚሞተው በኃጢአቱ ምክንያት ነው፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ጻድቁ ከጽ​ድቁ ቢመ​ለስ፥ ኀጢ​አ​ት​ንም በሠራ ጊዜ፥ በዚያ ቢሞት፥ እርሱ በአ​ደ​ረ​ገው በደል ይሞ​ታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ጻድቁ ከጽድቁ ቢመለስ፥ ኃጢአትንም በሠራ ጊዜ፥ በዚያም ቢሞት፥ እርሱ ባደረገው በደል ይሞታል።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 18:26
11 Referencias Cruzadas  

እነርሱም በጨለማ መንገድ ለመሄድ የቀናውን ጎዳና የሚተዉ፥


አባቱ ግን ፈጽሞ በድሎአልና፥ ወንድሙንም ቀምቶአልና፥ በሕዝቡም መካከል ክፉን ነገር አድርጎአልና እነሆ፥ እርሱ በበደሉ ይሞታል።


ጻድቁ ግን ከጽድቁ ቢመለስ፥ በደልንም ቢሠራ፥ ክፉ ሰው እንደሚያደርገው ርኩሰት ሁሉ ቢያደርግ፥ በሕይወት ይኖራልን? የሠራው ጽድቅ ሁሉ አይታሰብለትም፤ ታማኝ ባለመሆኑና በሠራው ኃጢአት በእነሱ ይሞታል።


እናንተ ግን፦ የጌታ መንገድ ቀና አይደለም ትላላችሁ። የእስራኤል ቤት ሆይ ስሙ፥ በውኑ መንገዴ ቀና አይደለምን? ቀና ያልሆነውስ የእናንተ መንገድ አይደለምን?


ክፉ ሰውም ከሠራው ክፋት ቢመለስ፥ ፍትሕንና ጽድቅንም ቢያደርግ ነፍሱን በሕይወት ያኖራል።


ጻድቁ ደግሞ ከጽድቁ ተመልሶ ኃጢአት ከሠራ፥ እኔም በፊቱ ዕንቅፋትን አደርጋለሁ፥ እርሱም ይሞታል፤ አንተም አላስጠነቀቅኸውምና በኃጢአቱ ይሞታል፥ የጽድቁም ሥራ አይታሰብለትም፥ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ።


እኔ ጻድቁን፦ በእርግጥ በሕይወት ትኖራለህ ባልሁት ጊዜ፥ እርሱ ጽድቁን ተማምኖ ኃጢአት ቢሠራ በሠራው ኃጢአትም ይሞታል እንጂ ጽድቁ አይታሰብለትም።


ጻድቅ ከጽድቁ ተመልሶ ኃጢአትን ቢሠራ በእነርሱ ይሞታል።


ካህኑም በጌታ ፊት ያስተሰርይለታል፥ ስለዚያም ስላደረገው በደል ሁሉ ይቅር ይባላል።”


ይህም የሚሆነው ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ ከሰማችሁትም ከወንጌል ተስፋ ሳትናወጡ በእምነት የምትጸኑ ከሆነ ነው፤ ይህም ወንጌል ከሰማይ በታች ባለው ፍጥረት ሁሉ ዘንድ የተሰበከ ነው፤ እኔም ጳውሎስ የእርሱ አገልጋይ ሆንሁ።


ዓመፃ ሁሉ ኃጢአት ነው፥ ለሞት የማያበቃ ኃጢአት አለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos