ሕዝቅኤል 17:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 ከፍ ባለው በእስራኤል ተራራ ላይ እተክለዋለሁ፥ ቅርንጫፎችም ያወጣል፥ ፍሬም ያፈራል፥ የተዋበ ዝግባ ይሆናል፥ በበታቹም ወፎች ሁሉ ይኖራሉ፥ በቅርንጫፎቹም ጥላ በክንፍ የሚበርሩ ሁሉ ይቀመጣሉ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም23 ከፍ ባለው የእስራኤል ተራራ ላይ እተክለዋለሁ፤ ቅርንጫፎች ያወጣል፤ ፍሬ ያፈራል፤ ያማረም ዝግባ ይሆናል። የወፍ ዐይነት ሁሉ መኖሪያውን በዚያ ያደርጋል፤ በቅርንጫፎቹም ጥላ ሥር ያርፋል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 የምተክለው በእስራኤል በሚገኝ በከፍተኛ ተራራ ላይ ነው፤ ይህንንም የማደርገው ቅርንጫፎችን አስገኝቶ ፍሬ በማፍራት የተዋበ የሊባኖስ ዛፍ እንዲሆን ነው። በሥሩም የተለያዩ ወፎች ይኖሩበታል፤ በቅርንጫፎቹም ጥላ ሥር ክንፍ ያላቸው ፍጥረቶች ሁሉ ጎጆዎቻቸውን ይሠሩበታል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 ከፍ ባለው በእስራኤል ተራራ ላይ እተክለዋለሁ፤ ቅርንጫፎችንም ያወጣል፤ ፍሬም ያፈራል፤ ታላቅም ዝግባ ይሆናል፤ በበታቹም ወፎች ሁሉ ያርፋሉ፤ በቅርንጫፎቹም ጥላ በክንፍ የሚበርር ሁሉ ይጠጋል፤ ቅርንጫፉም ይሰፋል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 ከፍ ባለው በእስራኤል ተራራ ላይ እተክለዋለሁ፥ ቅርንጫፎችም ያወጣል ፍሬም ያፈራል የከበረም ዝግባ ይሆናል፥ በበታቹም ወፎች ሁሉ ያርፋሉ፥ በቅርንጫፎቹም ጥላ በክንፍ የሚበርር ሁሉ ይጠጋል። Ver Capítulo |