Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 16:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በጌጥ አስጌጥሁሽ፥ በእጅሽ ላይ አንባር በአንገትሽም ላይ ሐብል አደረግሁልሽ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 በጌጣጌጥ አንቈጠቈጥሁሽ፤ በእጅሽ አንባር፣ በዐንገትሽም ድሪ አጠለቅሁልሽ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 በጌጥ አስጌጥኩሽ፤ የእጅ አንባርና የአንገት ድሪ አደረግሁልሽ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 በጌ​ጥም አስ​ጌ​ጥ​ሁሽ፤ በእ​ጅ​ሽም ላይ አን​ባር፥ በአ​ን​ገ​ት​ሽም ላይ ድሪ አደ​ረ​ግ​ሁ​ልሽ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በጌጥም አስጌጥሁሽ በእጅሽም ላይ አንባር በአንገትሽም ላይ ድሪ አደረግሁልሽ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 16:11
31 Referencias Cruzadas  

ግመሎቹም ከጠጡ በኋላ እንዲህ ሆነ፥ ሰውዬው ግማሽ ሰቅል የሚመዝን የወርቅ ቀለበት፥ ለእጆችዋም ዐሥር ሰቅል የሚመዘን ጥንድ የወርቅ አምባር አወጣ፥


እኔም፦ ‘አንቺ የማን ልጅ ነሽ?’ ብዬ ጠየቅኋት። እርሷም፦ ‘ሚልካ ለናኮር የወለደችለት የባቱኤል ልጅ ነኝ’ አለች፥ ቀለበትም አደረግሁላት፥ ለእጆችዋም አምባሮች አደረግሁላት።


ሎሌውም የብርና የወርቅ ጌጥ ልብስም አወጣ፥ ለርብቃም ሰጣት፥ የከበረ ስጦታንም ለወንድምዋና ለእናትዋ አቀረበ።


እነርሱም በእጃቸው ያሉትን ባዕዳን አማልክት ሁሉ፥ እንዲሁም በጆሮአቸውም ያሉትን ጉትቾች ለያዕቆብ ሰጡት፥ ያዕቆብም በሴኬም አጠገብ ካለችው የባሉጥ ዛፍ በታች ቀበራቸው።


ፈርዖንም ባለማኅተሙን ቀለበት ከጣቱ አውልቆ በዮሴፍ ጣት ላይ አደረገው፤ እንዲሁም ከጥሩ የተልባ እግር የተሠራ ልብስ አለበሰው፤ በዐንገቱም የወርቅ ሐብል አጠለቀለት።


ወንድሞቹና እኅቶቹ ቀድሞም ያውቁት የነበሩት ሁሉ ወደ እርሱ መጡ፥ በቤቱም ከእርሱ ጋር እንጀራ በሉ፥ ስለ እርሱም አዘኑለት፥ ጌታም ካመጣበት ክፉ ነገር ሁሉ አጽናኑት፥ እያንዳንዳቸውም ብርና የወርቅ ቀለበት ሰጡት።


አሮንም፦ “በሚስቶቻችሁ፥ በወንዶችና በሴቶች ልጆቻችሁ ጆሮ ያሉትን የወርቅ ቀለበቶች ሰብራችሁ አምጡልኝ” አላቸው።


ልባቸው የተነሣሣ ወንዶችና ሴቶች ሁሉ የአፍንጫ ጌጦችን፥ ሎቲዎችን፥ ቀለበቶችን፥ ድሪዎችን፥ የወርቅ ጌጦችን ሁሉ አመጡ፤ ሰዎች ሁሉ የወርቅ ስጦታ ለጌታ አመጡ።


ለራስህ የሞገስ ዘውድ ለአንገትህም ሐብል ይሆንልሃልና።


የሚሰማን ጆሮ የሚገሥጽ ጠቢባዊ ምክር፥ እንደ ወርቅ ጉትቻ እንደሚያንጸባርቅም ዕንቁ ነው።


በራስህ የጸጋ አክሊልን ታኖራለች፥ የተዋበ ዘውድንም ታበረክትልሃለች።”


የጉንጭሽ ውበት በከበረ ሉል፥ አንገትሽም በዕንቁ ድሪ ያማረ ነው።


እኅቴ ሙሽራ ሆይ፥ ልቤን በደስታ አሳበድሽው፥ አንድ ጊዜ በዐይኖችሽ፥ ከአንገትሽስ ድሪ በአንዱ ልቤን በደስታ አሳበድሽው።


በዚያ ቀን የሠራዊት ጌታ ለቀሩት ሕዝቡ የክብር ዘውድና የጌጥ አክሊል ይሆናል፤


የጆሮ ጉትቻውን፤ የእጅ አንባሩን፤ የፊት መሸፈኛውን፤


የጣት ቀለበቶችንና የአፍንጫ ቀለበቶችን፤


አክሊል ከራሳችን ወድቆአል፥ ኃጢአት ሠርተናልና ወዮልን!


የሰጠሁሽን ከወርቄና ከብሬ የተሠራውን የሚያምር ጌጣጌጥ ወስደሽ የወንድ ምስሎች ለራስሽ ሠራሽ፥ ከእነርሱም ጋር አመነዘርሽ።


ደግሞም መልእክተኛ ወደ ተላከባቸው፥ ከሩቅም ወደሚመጡ ሰዎች ልከዋል፥ እነሆም መጡ፤ ታጠብሽላቸው ዓይንሽን ተኳልሽ፥ ጌጥም አደረግሽ፤


የደስተኞችም ድምፅ በእርሷ ዘንድ ነበረ፥ ከብዙም ሰዎች ጉባኤ ጋር ሰካራሞቹ ከምድረበዳ መጡ፥ በእጃቸው አንበር በራሳቸውም የተዋበ አክሊል አደረጉ።


ደስታዋንም ሁሉ፥ በዓላቶችዋንም፥ መባቻዎችዋንም፥ ሰንበቶችዋንም፥ የተቀደሱትንም ጉባኤዎችዋን ሁሉ አስቀራለሁ።


ጌታም ሙሴን እንዳዘዘው በራሱ ላይ መጠምጠሚያውን አደረገ፤ በመጠምጠሚያውም ላይ በፊቱ በኩል፥ የወርቅ ጉንጉን ሆኖ በቅጠል መልክ የተሠራውን የተቀደሰ አክሊል፥ አደረገ።


ሰውም ሁሉ ካገኘው ከወርቅ ዕቃ፥ ከእግር አልቦም፥ ከአምባርም፥ ከቀለበትም፥ ከጉትቻም፥ ከወርቁም ጌጣጌጥ ለነፍሳችን በጌታ ፊት እንዲያስተሰርይልን ለጌታ መባ አምጥተናል።”


የሚጠብቅህን መከራ አትፍራ። እነሆ እንድትፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያስገባ ነው፤ ለዐሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ። እስከ ሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ።


ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም በሕይወት ለሚኖረው ይሰግዳሉ፤ አክሊላቸውንም በዙፋኑ ፊት አኑረው እንዲህ ይላሉ፥


በዙፋኑ ዙሪያም ሃያ አራት ዙፋኖች ነበሩ፤ በዙፋኖቹም ላይ ነጭ ልብስ ለብሰው በራሳቸውም የወርቅ አክሊል ደፍተው ሃያ አራት ሽማግሌዎች ተቀምጠው ነበር።


እርሱም “አንድ የምጠይቃችሁ ነገር አለኝ፤ ይኸውም እያንዳንዳችሁ ከምርኮ ካገኛችሁት ውስጥ የጆሮ ጉትቻችሁን እንድትሰጡኝ ነው” አላቸው፤ የወርቅ ጉትቻ ማድረግ የእስማኤላውያን ባህል ነበርና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos