Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 15:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 የሰው ልጅ ሆይ፥ በዱር ዛፎች መካከል ያለው የወይን ቅርንጫፍ፥ ከሁሉም ዛፎች ይልቅ የወይን ግንድ የሚበልጠው እንዴት ነው?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 “የሰው ልጅ ሆይ፤ የወይን ግንድ በዱር ካሉት ዛፎች ሁሉ ቅርንጫፍ የሚሻለው በምንድን ነው?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 “የሰው ልጅ ሆይ! የወይን ግንድ ከሌሎች ዛፎች ግንድ ቅርንጫፎች ከዱር ዛፎች ቅርንጫፍ በምን ይበልጣል?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 “የሰው ልጅ ሆይ! የወ​ይን ግንድ ከዱር ዛፎች ሁሉና ከዱር ዛፎች ቅር​ን​ጫ​ፎች ሁሉ ይልቅ ብል​ጫው ምን​ድን ነው?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2-3 የሰው ልጅ ሆይ፥ የወይን ግንድ፥ በዱር ዛፎች መካከል ያለ የወይን አረግ፥ ከዛፍ ሁሉ ይልቅ ብልጫው ምንድር ነው? በውኑ ሥራ የሚሠራበትን እንጨት ከእርሱ ይወስዳሉን? ወይስ ሰዎች ዕቃ የሚንጠለጠልበትን ኵላብ ከእርሱ ይወስዳሉን?

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 15:2
20 Referencias Cruzadas  

በለሱ ጐመራ፥ ወይኖችም አበቡ መዓዛቸውንም ሰጡ፥ ወዳጄ ሆይ፥ ተነሺ፥ ውቤ ሆይ፥ ነዪ።


ወይናችን አብቦአልና የወይናችንን ቦታ የሚያጠፉትን ቀበሮች፥ ትናንሾችን ቀበሮች አጥምዳችሁ ያዙልን።


የወንዙን ዳር ልምላሜ አይ ዘንድ፥ ወይኑ አብቦ ሮማኑም አፍርቶ እንደሆነ እመለከት ዘንድ ወደ ለውዝ ገነት ወረድሁ።


ወደ ወይኑ ቦታ ማልደን እንሂድ፥ ወይኑ አብቦ አበባውም ፍሬ አንዠርግጎ ሮማኑም አፍርቶ እንደሆነ እንይ፥ በዚያ ፍቅሬን እሰጥሃለሁ።


ሰማያት ሆይ፥ ጌታ አድርጎታልና ዘምሩ፤ ጌታ ያዕቆብን ተቤዥቶአልና፥ በእስራኤልም ዘንድ ይከበራልና አንተ የምድር ጥልቅ ሆይ፥ ጩኽ፤ እናንተም ተራሮች አንተም ዱር በአንተም ያለ ዛፍ ሁሉ፥ እልል በሉ።


እኔ የተመረጠች ወይን ፍጹምም እውነተኛ ዘር አድርጌ ተክዬሽ ነበር፤ አንቺ ግን የተበላሸ የእንግዳ ወይን ግንድ ሆነሽ እንዴት ተለወጥሽብኝ?


የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦


ማንኛውም ሥራ ለመስራት እንጨት ከእርሱ ይወስዳል? ወይስ ሰዎች ዕቃ የሚንጠለጠልበትን ኩላብ ከእርሱ ይወስዳሉን?


ነገር ግን በቁጣ ተነቀለች፥ ወደ መሬትም ተጣለች፤ የምሥራቅ ነፋስ ፍሬዋን አደረቀ፤ ብርቱ ቅርንጫፎቿም ተሰበሩና ደረቁ፤ እሳትም በላቸው።


እስራኤል ፍሬውን የሚሰጥ የተትረፈረፈ ወይን ነው፤ እንደ ፍሬው ብዛት መሠዊያዎችን አብዝቶአል፤ እንደ ምድሩም ብልጥግና መጠን ሐውልቶችን እያሳመሩ ሠርተዋል።


ስለዚህ በእናንተ ምክንያት ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፥ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፥ የቤቱም ተራራ የዱር ከፍታ ይሆናል።


የጥድ ዛፍ ሆይ፥ ዝግባ ወድቆአልና፥ የከበሩትም ዛፎች ጠፍተዋልና አልቅሱ! እናንተም የባሳን ዛፎች ሆይ፥ ጽኑው ጫካ ተቈርጦአልና አልቅሱ!


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos