ሕዝቅኤል 14:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 ነገር ግን እነሆ፥ የሚያመልጡና ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን የሚያወጡ ይቀሩላታል፥ እነሆ ወደ እናንተ ይመጣሉ፥ እናንተም መንገዳቸውንና ሥራቸውን ታያላችሁ፥ በኢየሩሳሌም ላይ ስላመጣሁት ክፉ ነገር፥ ስላመጣሁባትም ነገር ሁሉ ትጽናናላችሁ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 ነገር ግን ከዚያ ወጥተው የሚተርፉ ወንዶችና ሴቶች ልጆች አሉ፤ እነርሱም ወደ እናንተ ይመጣሉ፤ እናንተም አካሄዳቸውንና ተግባራቸውን በምታዩበት ጊዜ፣ በኢየሩሳሌም ላይ ስላመጣሁት መከራ፣ ስላደረስሁባትም አስከፊ ነገር ሁሉ ትጽናናላችሁ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22-23 ሆኖም በኢየሩሳሌም ውስጥ ከእርስዋ ወደ እናንተ የሚመጡ ቅሬታዎች ይቀሩላታል፤ አካሄዳቸውንና ተግባራቸውን በምታዩበት ጊዜ የእነርሱን ሁኔታ ትረዳላችሁ፤ እናንተም በእነርሱ ላይ ያደረስኩት መቅሠፍት ሁሉ ያለምክንያት እንዳልሆነ ታውቃላችሁ።” ይላል ልዑል እግዚአብሔር። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 ነገር ግን እነሆ የሚያመልጡና ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ከእርስዋ የሚያወጡ ይቀሩላታል፤ እነሆ ወደ እናንተ ይወጣሉ፤ እናንተም መንገዳቸውንና ሥራቸውን ታያላችሁ፤ በኢየሩሳሌምም ላይ ስላመጣሁት ክፉ ነገር ሁሉ፥ ስላመጣሁባትም ነገር ሁሉ ትጽናናላችሁ፤ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 ነገር ግን፥ እነሆ፥ የሚያመልጡና ወንዶችና ሴቶች ልጆችን የሚያመጡ ይቀሩላታል፥ እነሆ፥ ወደ እናንተ ይወጣሉ እናንተም መንገዳቸውንና ሥራቸውን ታያላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም ላይ ስላመጣሁት ክፉ ነገር ሁሉ ስላመጣሁባትም ነገር ሁሉ ትጽናናላችሁ። Ver Capítulo |