Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 14:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 እነዚህ ሦስት ሰዎች በውስጧ ቢኖሩ፥ እኔ ሕያው ነኝና ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ እነርሱ ብቻቸውን ይድናሉ እንጂ ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻቸውን አያድኑም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 በሕያውነቴ እምላለሁ ይላል እግዚአብሔር፤ እነዚህ ሦስት ሰዎች ቢኖሩባትም እንኳ ራሳቸው ብቻ ይድናሉ እንጂ ወንዶች ወይም ሴቶች ልጆቻቸውን ማዳን አይችሉም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እኔ እግዚአብሔር ሕያው አምላክ እንደ መሆኔ እነዚያ ሦስት ሰዎች እንኳ በዚያ ቢገኙ ከራሳቸው ሕይወት በቀር የገዛ ልጆቻቸውን እንኳ ማዳን አይችሉም፤ ይላል ልዑል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እነ​ዚህ ሦስት ሰዎች በመ​ካ​ከ​ልዋ ቢኖሩ፥ እኔ ሕያው ነኝ! እነ​ርሱ ብቻ​ቸ​ውን ይድ​ናሉ እንጂ ወን​ዶ​ች​ንና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን አያ​ድ​ኑም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እነዚህ ሦስት ሰዎች ቢኖሩባት እኔ ሕያው ነኝና እነርሱ ብቻቸውን ይድናሉ እንጂ ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻቸውን አያድኑም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 14:18
6 Referencias Cruzadas  

እነርሱ ግን ነቢያት ቢሆኑ፥ የጌታም ቃል በእነርሱ ዘንድ ቢገኝ፥ በጌታ ቤትና በይሁዳ ንጉሥ ቤት በኢየሩሳሌምም የቀሩት ዕቃዎች ወደ ባቢሎን እንዳይሄዱ እስቲ ወደ ሠራዊት ጌታ ይማለሉ።


በአሕዛብ መካከል ስበትናቸው፥ በአገሮችም ስዘራቸው፥ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


ኖኅ ዳንኤልና ኢዮብ እነዚህ ሦስት ሰዎች፥ በውስጧ ቢኖሩ እንኳ በጽድቃቸው የገዛ ነፍሳቸውን ያድናሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


እነዚህ ሦስት ሰዎች በውስጧ ቢኖሩ፥ እኔ ሕያው ነኝና ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ እነርሱ ብቻቸውን ይድናሉ እንጂ ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻቸውን አያድኑም፥ ምድሪቱም ባድማ ትሆናለች።


ወይም በዚያች ምድር ላይ ሰይፍ አምጥቼ፦ በምድሪቱ ላይ ሰይፍ ይለፍ ብል፥ ሰውንና እንስሳን ከእርሷ ባጠፋ፥


ወይም በዚያች ምድር ላይ ቸነፈር ብሰድድ፥ ቁጣዬን በደም ባፈስስባትና ሰውንና እንስሳንም ከእርሷ ባጠፋ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos