ዘፀአት 9:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 እነሆ የጌታ እጅ በሜዳ ውስጥ ባሉት በከብቶችህ፥ በፈረሶች፥ በአህዮች፥ በግመሎች፥ በበሬዎችና በበጎች ላይ ትሆናለች፤ ብርቱ ተላላፊ በሽታ ይወርዳል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 የእግዚአብሔር እጅ በመስክ ላይ ባሉት እንስሳት፣ በፈረሶችህና በአህዮችህ፣ በግመሎችህና በቀንድ ከብቶችህ፣ በበጎችህና በፍየሎችህ ላይ አስከፊ መቅሠፍት ያመጣብሃል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 የእግዚአብሔር እጅ በመስክ የሚገኘውን መንጋህን ማለት ፈረሶችህን፥ አህዮችህን፥ ግመሎችህን፥ የቀንድ ከብቶችህን፥ በጎችህንና ፍየሎችህን በታላቅ መቅሠፍት ይመታል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 እነሆ፥ የእግዚአብሔር እጅ በሜዳ ውስጥ በአሉት በከብቶችህ፥ በፈረሶችም፥ በአህዮችም፥ በግመሎችም፥ በበሬዎችም፥ በበጎችም ላይ ትሆናለች፤ ይኸውም እጅግ ጽኑዕ ሞት ነው፤ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 እነሆ የእግዚአብሔር እጅ በሜዳ ውስጥ ባሉት በከብቶችህ፥ በፈረሶችም በአህዮችም፥ በግመሎችም፥ በበሬዎችም፥ በበጎችም ላይ ትሆናለች፤ ብርቱ ቸነፈርም ይወርዳል። Ver Capítulo |