ዘፀአት 5:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 ቀድሞ ይሠሩት የነበረውን የጡብ ቍጥር በእነርሱ ላይ አድርጉት፤ ከእርሱ አታጉድሉ፤ ሥራ ሰልችተዋልና ስለዚህ፦ ‘ለአምላካችን እንድንሰዋ መሄድ እንፈልጋለን’ እያሉ ይጮኸሉ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 ሆኖም ቀድሞ በሚያቀርቡት ሸክላ ልክ ሠርተው እንዲያቀርቡ አድርጓቸው። የሥራ ድርሻቸውን አትቀንሱ። ሰነፎች ናቸው፤ ‘ሄደን ለአምላካችን መሥዋዕት እንሠዋ’ የሚሉትም ለዚህ ነው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 ነገር ግን ቀድሞ ይሠሩት የነበረውን ያኽል አንድ ጡብ እንኳ ሳይጐድል እንዲያስረክቡ አድርጉ፤ ‘ለአምላካችን መሥዋዕት እናቀርብ ዘንድ ልቀቀን!’ እያሉ የሚነዘንዙኝ ብዙ የሚሠሩት ነገር ስለሌለ ነው፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 ቀድሞ ያደርጉት የነበረውን የጡብ ቍጥር እንዲሁ በየቀኑ በእነርሱ ላይ አድርጉት፤ ምንም ከእርሱ አታጕድሉ፤ ሥራ ሰልችተዋልና ስለዚህ፦ ‘ለአምላካችን እንድንሠዋ እንሂድ’ እያሉ ይጮሃሉ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 ቀድሞ ያደርጉት የነበረውን የጡብ ቁጥር በእነርሱ ላይ አድርጉት፤ ምንም ከእርሱ አታጉድሉ፤ ሥራ ሰልችተዋልና ስለዚህ፥ ‘ለአምላካችን እንድንሰዋ እንሂድ’ እያሉ ይጮኻሉ። Ver Capítulo |