ዘፀአት 4:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 የጌታም ቁጣ በሙሴ ላይ ነደደ እንዲህም አለ፦ “ሌዋዊው ወንድምህ አሮን አለ አይደለምን? እርሱ ጥሩ እንደሚናገር አውቃለሁ፤ እርሱም ደግሞ ሊገናኝህ ይመጣል፤ ያይሃልም፤ በልቡም ደስ ይለዋል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር ቍጣ በሙሴ ላይ ነደደ፤ “ሌዋዊው ወንድምህ አሮን አለ አይደል? እርሱ ጥሩ እንደሚናገር ዐውቃለሁ፤ እንዲያውም አሁን ወደ አንተ እየመጣ ነው፤ በሚያይህም ጊዜ ከልቡ ደስ ይለዋል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር ሙሴን እጅግ ተቈጥቶ እንዲህ አለው፤ “ሌዋዊ የሆነው ወንድምህ አሮን አለ አይደለምን? እርሱ ጥሩ ተናጋሪ መሆኑን ዐውቃለሁ፤ እንዲያውም አሁን ወደ አንተ እየመጣ ነው፤ በሚያይህም ጊዜ ከልብ ደስ ይለዋል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 እግዚአብሔርም በሙሴ ላይ እጅግ ተቈጣ፤ እንዲህም አለ፥ “ሌዋዊው ወንድምህ አሮን አለ አይደለምን? እርሱ እንደሚናገርልህ አውቃለሁ፤ እነሆም፥ እርሱ ሊገናኝህ ይመጣል፤ በአየህም ጊዜ በልቡ ደስ ይለዋል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 የእግዚአብሔርም ቍጣ በሙሴ ላይ ነደደ እንዲህም አለ፦ “ሌዋዊው ወንድምህ አሮን አለ አይደለምን? እርሱ ደህና እንዲናገር አውቃለሁ፤ እነሆም ደግሞ ሊገናኝህ ይመጣል፤ ባየህም ጊዜ በልቡ ደስ ይለዋል። Ver Capítulo |