Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 39:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 የሸማኔ ሥራ ከጥሩ በፍታ ለአሮንና ለልጆቹ ቀሚስ አዘጋጁ፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ የሸማኔ ሥራ የሆነውን ከቀጭን በፍታ ሸሚዞችን ሠሩ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ለአሮንና ለልጆቹ የሚከተሉትን ልብሶች አዘጋጁ፤ ሸማኔ ከሠራው ከጥሩ በፍታ ሸሚዞችን፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 እንደ ሸማኔ ሥራ ከጥሩ በፍታ ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ እጀ ጠባ​ቦ​ችን፥ ከጥሩ በፍ​ታም አክ​ሊ​ልን፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው፥ እንደ ሸማኔ ሥራ ከጥሩ በፍታ ለአሮንና ለልጆቹ ሸሚዞችን፥

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 39:27
14 Referencias Cruzadas  

በራሳቸው ላይ የተልባ እግር መጠምጠሚያ ይሁን፥ በወገባቸውም ላይ የተልባ እግር ሱሪ ይሁን፤ የሚያልብ ነገር አይታጠቁ።


ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኖራችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ።


ከክርስቶስ ጋር አንድ ለመሆን የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችሁታል።


ነገር ግን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ የሥጋም ሐሳብ ምኞቱን እንዲፈጽም አትፍቀዱለት።


ይህ የእግዚአብሔር ጽድቅ ለሚያምኑ ሁሉ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ባለን እምነት የሚገኝ ነው፤ ልዩነት የለምና፤


አክሊልን እንደ ለበሰ ሙሽራ፥ በጌጥ ሽልማትዋም እንዳጌጠች ሙሽራ፥ የማዳንን ልብስ አልብሶኛልና፥ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛልና በጌታ እጅግ ደስ ይለኛል፥ ነፍሴም በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች።


ጌታም ሙሴን እንዳዘዘው ሙሴ የአሮንን ልጆች አቀረበ፥ ቀሚሶችንም አለበሳቸው፥ በመርገፍም በተጌጠ መታጠቂያ አስታጠቃቸው፥ ቆብም ደፋባቸው።


ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው ለማገልገል በቀሚሱ ዘርፍ ዙሪያ ሻኩራና ሮማን፥ ሻኩራና ሮማን አደረጉ።


ከጥሩ በፍታ መጠምጠሚያውን፥ ከጥሩ በፍታም ቆቦች፥ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ ሱሪዎችን ሠሩ፥


ካህኑም ሰውነቱን ለመሸፈን የበፍታ ቀሚስና የበፍታ ሱሪ ይለብሳል፤ በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት እሳቱ ከበላው በኋላ አመዱን አንሥቶ በመሠዊያው አጠገብ ያፈስሰዋል።


ወደ ውስጠኛው አደባባይ በር በገቡ ጊዜ የተልባ እግር ልብስ ይልበሱ፤ በውስጠኛው አደባባይ በርና በቤቱ ውስጥ ባገለገሉ ጊዜ አንዳች የበግ ጠጉር በላያቸው አይሁን።


ከንጹህ ወርቅ ቅጠል ሥራ፥ በእርሱም ላይ እንደ ማኅተም ቅርጽ ‘ለጌታ የተቀደሰ’ የሚል ቅረጽበት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios