Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 39:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው ለማገልገል በቀሚሱ ዘርፍ ዙሪያ ሻኩራና ሮማን፥ ሻኩራና ሮማን አደረጉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ለአገልግሎት ይለበሱ ዘንድ ሻኵራዎቹና ሮማኖቹ በቀሚሱ ጠርዝ ዙሪያ ላይ ተሰባጥረው ይገኙ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት መርገፎቹ የሮማን ፍሬ፥ በልብሱ ግርጌ ዙሪያ አከታትለው አደረጉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 በቀ​ሚሱ ዘርፍ ዙሪያ ሻኵ​ራ​ንና ሮማ​ንን፥ ሻኩ​ራ​ንና ሮማ​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ለማ​ገ​ል​ገል አደ​ረጉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 በቀሚሱ ዘርፍ ዙሪያ ሻኵራንና ሮማንን፥ ሻኵራንና ሮማንን ለማገልገል አደረጉ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 39:26
9 Referencias Cruzadas  

የወርቅ ሻኩራና ሮማን፥ የወርቅ ሻኩራና ሮማን በቀሚሱ ዘርፍ ዙሪያውን ይሆናሉ።


እነሆ ለዐሥራ ሁለት ዓመታት ደም የሚፈስሳት ሴት ከኋላው ተጠግታ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፤


በዓይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ጉንጭና ጉንጭሽ እንደ ተከፈለ ሮማን ናቸው።


ቡቃያሽ ሮማንና የተመረጠ ፍሬ፥ ዕፀ ሕና ከናርዶስ ጋር ያለበት ገነት ነው፥


ከንፈሮችሽ እንደ ቀይ ሐር ፈትል ናቸው፥ አፍሽም ያማረ ነው፥ በመሸፈኛሽ ውስጥ ጉንጭና ጉንጭሽ እንደ ተከፈለ ሮማን ናቸው።


“በምትለብሰው በልብስህ በአራቱ ማዕዘን ዘርፍ አድርግ።


በታችኛው ዘርፍ ዙሪያ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃ ሮማኖች አድርግ፤ በዚያም መካከል በዙሪያው የወርቅ ሻኩራዎች አድርግ፤


ከንጹሕ ወርቅ ሻኩራዎችን ሠሩ፥ ሻኩራዎቹንም በሮማኖቹ መካከል በቀሚሱ ዘርፍ ዙሪያ አደረጉ።


የሸማኔ ሥራ ከጥሩ በፍታ ለአሮንና ለልጆቹ ቀሚስ አዘጋጁ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios