ዘፀአት 35:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 ስድስት ቀን ሥራህን ትሠራለህ፥ ሰባተኛው ቀን ግን ለጌታ የዕረፍት፥ ለእናንተ የተቀደሰ ሰንበት አለለችሁ፥ በዚህ ቀን የሚሠራበትም ሁሉ ይገደል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 ስድስት ቀን ሥራ ይሠራል፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር የሰንበት ዕረፍት፣ የተቀደሰ ቀን ይሆንላችኋል፤ በዕለቱ ማንኛውንም ዐይነት ሥራ የሚሠራ ቢኖር ሞት ይገባዋል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 ሥራችሁን ሁሉ የምትሠሩባቸው ስድስት ቀኖች አሉላችሁ፤ ሰባተኛው ቀን ግን ዕረፍት ታደርጉበት ዘንድ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ዕለት ነው፤ በዚህ ቀን ሥራ የሚሠራበት ማንኛውም ሰው በሞት ይቀጣል፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 ስድስት ቀን ሥራህን ትሠራለህ፤ በሰባተኛው ቀን ታርፋለህ፤ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ የዕረፍት ሰንበት ነው፤ የሚሠራበትም ሁሉ ይሙት። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር የዕረፍት ሰንበት የተቀደሰ ቀን ይሆንላችኋል፤ የሚሰራበትም ሁሉ ይገደል። Ver Capítulo |