Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 32:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 አሁንም ሂድ፥ ይህንንም ሕዝብ ወደ ነገርኩህ ስፍራ ምራ፤ እነሆ መልአኬ በፊትህ ይሄዳል፤ ነገር ግን በምጐበኝበት ቀን ኃጢአታቸውን በላያቸው ላይ አመጣባቸዋለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 አሁን ሂድ፤ ሕዝቡን ወደ ተናገርሁት ስፍራ ምራው፤ መልአኬም በፊትህ ይሄዳል፤ ሆኖም የምቀጣበት ጊዜ ሲደርስ፣ ስለ ኀጢአታቸው እቀጣቸዋለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 አሁንም ሂድ፤ ወደነገርኩህ ስፍራ ሕዝቡን ምራ፤ መልአኬም እየመራህ በፊትህ እንደሚሄድ አስታውስ፤ ነገር ግን ይህን ሕዝብ ስለ ኃጢአቱ የምቀጣበት ጊዜ መምጣቱ አይቀርም።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 አሁ​ንም ሂድ፤ ይህ​ንም ሕዝብ ወደ ነገ​ር​ሁህ ቦታ ምራ፤ እነሆ፥ መል​አኬ በፊ​ትህ ይሄ​ዳል፤ ነገር ግን በም​ጐ​በ​ኝ​በት ቀን ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን አመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 አሁንም ሂድ፥ ይህንም ሕዝብ ወደ ነገርሁህ ምራ፤ እነሆ መልአኬ በፊትህ ይሄዳል፤ ነገር ግን በምግአበኝበት ቀን ኃጢአታቸውን አመጣባቸዋለሁ አለው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 32:34
21 Referencias Cruzadas  

በቀልና ብድራት መመለስ የእኔ ነው፤ እግራቸው የሚሰናከልበት ጊዜው፥ የመጥፊያቸው ቀን ቀርቧልና፥ የሚመጣባቸው ፍርድ ይፈጥናል።


“በመንገድ እንዲጠብቅህ፥ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ እንዲያስገባህ፥ እነሆ፥ እኔ መልአክን በፊትህ እልካለሁ።


በዚህም ምክንያት ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደሱና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው ጻድቅ ደም ሁሉ በእናንተ ላይ ይደርሳል።


“እስራኤልን ስለ ኃጢአቱ በምበቀልበት ቀን የቤቴልን መሠዊያዎች ደግሞ እበቀላለሁ፤ የመሠዊያውም ቀንዶች ይሰበራሉ፥ ወደ ምድርም ይወድቃሉ።


በውኑ ስለ እነዚህ ነገሮች አልቀሥፍምን? ይላል ጌታ፤ ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን?


በውኑ ስለ እነዚህ ነገሮች አልቀሥፍምን? ይላል ጌታ፤ ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን?


በጭንቃቸው ሁሉ እርሱ ተጨነቀ፥ የፊቱም መልአክ አዳናቸው፤ በፍቅሩና በርኅራኄውም ተቤዣቸው፥ በቀደመውም ዘመን ሁሉ አንሥቶ ተሸከማቸው።


አቤቱ አምላክችን ሆይ፥ አንተ ሰማሃቸው፥ አቤቱ፥ አንተ ማርሃቸው፥ ጥፋታቸውን ሁሉ ግን ተበቀልሃቸው።


ወደ ጌታም በጮኽን ጊዜ ድምፃችንን ሰማ፥ መልአክንም ልኮ ከግብጽ አወጣን፤ እነሆም፥ በምድርህ ዳርቻ ባለችው ከተማ በቃዴስ ተቀምጠናል።


በፊትህ መልአክ እልካለሁ፥ ከነዓናዊውን፥ አሞራዊውን፥ ኬጢያዊውን፥ ፌርዛዊውን፥ ኤዊያዊውንና ኢያቡሳዊውን አወጣልሃለሁ።


አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውም፤ እኔ ጌታ አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፥


ከግብጽም መከራ ወደ ከነዓናውያን ወደ ኬጢያውያንም ወደ አሞራውያንም ወደ ፌርዛውያንም ወደ ኤዊያውያንም ወደ ኢያቡሳውያንም አገር ወተትና ማር ወደምታፈስስ አገር አወጣችኋለሁ።’


አንተ ታመጣቸዋለህ፥ በርስትህም ተራራ ትተክላቸዋለህ፥ ጌታ ሆይ ለማደሪያህ በሠራኸው ስፍራ፥ ጌታ ሆይ እጆችህ ባዘጋጁት መቅደስ።


ሙሴ ጌታን እንዲህ አለው፥ “እይ! አንተ ‘ይህን ሕዝብ አውጣ’ ብለኸኛል፥ ነገር ግን ከእኔ ጋር የምትልከውን አላስታወቅኸኝም። አንተም፦ ‘በስምህ አወቅሁህ፥ ደግሞም በእኔ ፊት ሞገስን አግኝተሃል’ ብለኸኝ ነበር።


ስለዚህ የእስራኤል አምላክ ጌታ ሕዝቤን ስለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፦ “እናንተ በጎቼን በትናችኋል አባርራችኋቸዋልም አልጐበኛችኋቸውምም፤ እነሆ፥ ስለ ክፉ ሥራችሁ እጐበኛችኋለሁ፥ ይላል ጌታ።


ጌታ ለዚህ ሕዝብ እንዲህ ይላል፦ “በእውነት መቅበዝበዝን ወድደዋል፥ እግራቸውንም አልከለከሉም፤ ስለዚህ ጌታ በእነርሱ ደስ አይሰኝም፥ በደላቸውንም አሁን ያስታውሳል ስለ ኃጢአታቸውም ይቀጣቸዋል።”


የተመረጠውን መሥዋዕቴን ያቀርባሉ፥ ሥጋንም ያርዳሉ፥ ይበላሉም፤ ጌታ ግን በእነርሱ ደስ አይሰኝም፤ በደላቸውን አሁን ያስታውሳል፥ ስለ ኃጢአታቸውም ይቀጣቸዋል፤ እነርሱም ወደ ግብጽ ይመለሳሉ።


እንዲህም ይላል፦ “እኔ ከምድር ወገኖች ሁሉ እናንተን ብቻ አውቄአችኋለሁ፤ ስለዚህ ስለ ኃጢአታችሁ ሁሉ እበቀላችኋለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios