Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 29:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ለአሮን የክህነት ሥርዓት የታረደውን በግ ፍርምባ ወስደህ ለሚወዘወዝ ቁርባን በጌታ ፊት ትወዘውዘዋለህ፤ እርሱም የአንተ ድርሻ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ለአሮን ክህነት የአውራ በጉን ፍርምባ ከወሰድህ በኋላ እንደሚወዘወዝ መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት ወዝውዘው፤ ይህም የአንተ ድርሻ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 “ለአሮን ክህነት ሥርዓት ከታረደው የበግ አውራ ፍርምባውን ወስደህ ለእኔ ለእግዚአብሔር በመወዝወዝ የሚቀርብ መባ አድርገህ አንሣ፤ ይህም ለእናንተው የሚመደብ ድርሻ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 “ለአ​ሮ​ንም ክህ​ነት የታ​ረ​ደ​ውን የአ​ው​ራ​ውን በግ ፍር​ምባ ወስ​ደህ ለሚ​ለይ ቍር​ባን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ትለ​የ​ዋ​ለህ፤ እር​ሱም የአ​ንተ ወግ ይሆ​ናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ለአሮንም ክህነት የታረደውን በግ ፍርምባ ወስደህ ለሚወዘወዝ ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ትወዘውዘዋለህ፤ እርሱም የአንተ ወግ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 29:26
8 Referencias Cruzadas  

ሙሴና አሮን በካህናቱ ዘንድ፥ ሳሙኤልም ስሙን በሚጠሩት ዘንድ ናቸው፥ ጌታን ጠሩት፥ እርሱም መለሰላቸው።


ለክህነት ሥርዓት ከቀረበው አውራ በግ የተወሰደ ለአሮንና ለልጆቹ ድርሻ የሚሆን ለመሥዋዕት የተወዘወዘውን ፍርምባና የተነሣውን ወርች ትቀድሳለህ።


ካህኑም አንዱን ተባት ጠቦት ይወስዳል፤ እርሱንም ስለ በደል መሥዋዕት ያቀርበዋል፥ ጎን ለጎንም ዘይቱ ያለበትን የሎግ መስፈሪያውን፤ እነርሱንም ስለ መወዝወዝ ቁርባን በጌታ ፊት ይወዘውዛቸዋል።


የእርሱ እጆች ለጌታ በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን ያመጣሉ፤ እርሱም ፍርምባው በጌታ ፊት ለመወዝወዝ ቁርባን እንዲወዘወዝ ፍርምባውን ከስቡ ጋር ያመጣዋል።


ካህኑም ስቡን በመሠዊያው ላይ ያቃጥላል፤ ፍርምባው ግን ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናል።


የሚወዘወዘውን ፍርምባና እንደ ቁርባን የሚቀርበውን ወርች ከእስራኤል ልጆች ከሰላም መሥዋዕታቸው ወስጄ፥ ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹም ለዘለዓለም ድርሻ እንዲሆን ከእስራኤል ልጆች ዘንድ እነርሱን ሰጥቼአቸዋለሁ።


ሙሴም ፍርምባውን ወስዶ በጌታ ፊት ለመወዝወዝ ቁርባን ወዘወዘው፤ ጌታም ሙሴን እንዳዘዘው ይህ ለቅድስና ከሚቀርበው አውራ በግ የሆነ የሙሴ ድርሻ ነበር።


ሙሴም እንደ ታዘዘው አሮን ፍርምባዎቹንና ቀኝ ወርቹን በጌታ ፊት ለመወዝወዝ ቁርባን ወዘወዘ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos