Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 25:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ከግራር እንጨት መሎጊያዎችን ሥራ፥ በወርቅም ለብጣቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ከዚያም መሎጊያዎችን ከግራር ዕንጨት ሥራ፤ በወርቅም ለብጣቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ለታቦቱ መሸከሚያ የሚሆኑ መሎጊያዎችንም ከግራር እንጨት ሥራ፤ በወርቅም ለብጣቸው፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ች​ንም ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት ሥራ፤ በወ​ር​ቅም ለብ​ጣ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 መሎጊያዎችንም ከግራር እንጨት ሥራ፥ በወርቅም ለብጣቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 25:13
14 Referencias Cruzadas  

ሙሴም እንዳዘዘው እንደ ጌታ ቃል የሌዋውያን ልጆች የእግዚአብሔርን ታቦት በትከሻቸው ላይ በመሎጊያዎቹ ተሸከሙ።


በእርሱም ላይ የሚገለገሉባቸውን የመሠውያውን ዕቃዎች ሁሉ፥ ጀሞዎቹን ሜንጦቹንም መጫሪያዎቹንም ጐድጓዳ ሳሕኖቹንም፥ የመሠዊያውን ዕቃ ሁሉ ያስቀምጡበት፤ በእርሱም ላይ የአቆስጣን ቁርበት መሸፈኛ ይዘርጉ፥ መሎጊያዎቹንም ያግቡ።


በወርቁም መሠዊያ ላይ ሰማያዊውን መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፥ በአቆስጣም ቁርበት መሸፈኛ ይሸፍኑት፥ መሎጊያዎቹንም ያግቡ።


በእነርሱም ላይ ቀይ መጐናጸፊያ ይዘርጉ፥ በአስቆጣውም ቁርበት መሸፈኛ ይሸፍኑት፥ መሎጊያዎቹንም ያግቡ።


በእርሱም ላይ የአስቆጣውን ቁርበት መሸፈኛ ያድርጉበት፥ ከእርሱም በላይ ሁለንተናው ሰማያዊ የሆነ መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፥ መሎጊያዎቹንም ያግቡ።


ጽላቱን ወስዶ በታቦቱ ውስጥ አኖረው፥ መሎጊያዎቹንም በታቦቱ አደረገ፥ የስርየት መክደኛውንም በታቦቱ ላይ አኖረው፤


መሎጊያዎችን ከግራር እንጨት ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው።


መሎጊያዎቹን ከግራር እንጨት ሠርተህ በወርቅ ለብጣቸው።


ለመሠዊያው ከግራር እንጨት መሎጊያዎችን ሥራ፥ በነሐስም ለብጣቸው።


ገበታውን እንዲሸከሙባቸው መሎጊያዎቹን ከግራር እንጨት ሠርተህ በወርቅ ለብጣቸው።


ቀይ የተለፋ የአውራ በግ ቁርበት፥ የአስቆጣ ቁርበት፥ የግራር እንጨት፥


አራት የወርቅ ቀለበቶችም አድርግለት፥ እነርሱንም በአራቱ እግሮቹ ላይ አኑር፤ በአንድ ወገን ሁለት ቀለበቶች፥ በሌላው ወገን ሁለት ቀለበቶች ይሁኑ።


ታቦቱን በእነርሱ ለመሸከም በታቦቱ ጎን ባሉት ቀለበቶች መሎጊያዎቹን አስገባ።


መሎጊያዎቹ ረጃጅሞች ስለ ሆኑ ጫፎቻቸው በቤተ መቅደሱ ውስጥ በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት ይታይ ነበር፤ በውጭ በኩል ግን አይታዩም፤ እስከ ዛሬ ድረስም በዚያው ይገኛሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios