Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 23:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ጉቦን አትቀበል፤ ጉቦ የሚያዩ ሰዎችን ያሳውራልና፥ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “ጕቦ አትቀበል፤ ጕቦ አጥርተው የሚያዩትን ሰዎች ዐይን ያሳውራል፤ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ሰዎች ትክክለኛ የሆነውን ነገር እንዳያዩ ዐይናቸውን ስለሚያሳውርና የንጹሕ ሰዎችንም ፍርድ ስለሚያጣምም ጉቦ አትቀበል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 መማ​ለ​ጃን አት​ቀ​በል፤ መማ​ለጃ የዐ​ይ​ና​ማ​ዎ​ችን ዐይን ያሳ​ው​ራ​ልና፥ እው​ነ​ተኛ ቃል​ንም ያጣ​ም​ማ​ልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ማማለጃን አትቀበል፤ ማማለጃ የዓይናማዎችን ሰዎች ዓይን ያሳውራልና፥ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 23:8
20 Referencias Cruzadas  

ፍርድ አታዛባ፤ አድልዎ አታድርግ፤ ጉቦ የጠቢባንን ዐይን ያሳውራል፤ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና ጉቦም አትቀበል።


ጉቦን በመቀበል በደለኛን ንጹሕ ለሚያደርጉ፤ ለበደል አልባ ሰው ፍትሕን ለሚነፍጉ ወዮላቸው!


ኀጥእ የፍርድን መንገድ ለማጥመም ከብብት መማለጃን ይወስዳል።


ትርፍ ለማግኘት የሚሳሳ ሰው የራሱን ቤት ያውካል፥ መማለጃን የሚጠላ ግን በሕይወት ይኖራል።


ልጆቹ ግን የአባታቸውን ፈለግ አልተከተሉም፤ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ ከመንገዱ ወጡ፤ ጉቦ ተቀበሉ፤ ፍርድም አጣመሙ።


ግፍ ጠቢቡን ያሳብደዋል፥ ጉቦም ልቡን ያጠፋዋል።


ገንዘብ ባደረገው ፊት መማለጃ እንደ ተዋበ ዕንቁ ነው፥ ወደ ዞረበትም ስፍራ ሁሉ ሥራውን ያቀናል።


በእጃቸው ተንኰል አለባቸው፥ ቀኛቸውም በጉቦ ተሞልታለች።


እነሆ፤ ከፊታችሁ ቆሜአለሁ፤ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ፤ የማንን በሬ ወሰድሁ? የማንን አህያ ወሰድሁ? ማንን አታለልሁ? በማንስ ላይ ግፍ ሠራሁ? አይቶ እንዳላየ ለመሆንስ ከማን እጅ ጉቦ ተቀበልሁ? ከእነዚህ ሁሉ አንዱን እንኳ አድርጌ ከሆነ እመልስላችኋለሁ።”


ምክንያቱም ጌታ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ፥ የጌቶችም ጌታ፥ ታላቅ አምላክ፥ ኃያልም፥ የሚያስፈራም፥ በፍርድ የማያደላ፥ ጉቦም የማይቀበል ነው።


እጆቻቸው ክፉ ለማድረግ የተለማመዱ ናቸው፤ ልዑሉና ፈራጁ ጉቦን ይፈልጋሉ፥ ትልቁም ሰው እንደ ነፍሱ ምኞት ይናገራል፤ እንዲሁም ክፋትን ይጐነጉናሉ።


ጻድቁን የምታሠቃዩ፥ ጉቦንም የምትቀበሉ፥ በበሩም አደባባይ የችግረኛውን ፍርድ የምታጣምሙ እናንተ ሆይ! በደላችሁ እንዴት እንደ በዛ፥ ኃጢአታችሁም እንዴት እንደ ጸና እኔ አውቃለሁና።


ደም ለማፍሰስ በአንቺ ውስጥ ጉቦን ተቀበሉ፥ አንቺም አራጣና ትርፍ ወስደሻል፥ ጎረቤቶችሽንም ጨቁነሽ የማይገባ ትርፍ አገኘሽ፥ እኔንም ረሳሽኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ባለጠግነት ብዙ ወዳጆች ይጨምራል፥ የድሀ ወዳጅ ግን ከእርሱ ይርቃል።


ስካራቸውን ፈጽመዋል፥ ለምንዝርናም ራሳቸውን ፍጹም አስገዝተዋል፤ ከክብራቸው ይልቅ ውርደታቸውን እጅግ ወድደዋል።


ከንቱውን መባ አታቅርቡ፤ ዕጣናችሁን እጸየፋለሁ፤ የወር መባቻ በዓላችሁን፤ ሰንበቶቻችሁን፤ ጉባኤያችሁንና በክፋት የተሞላውን ስብሰባችሁን መታገሥ አልቻልሁም።


ገንዘቡን በአራጣ የማያበድር፥ በንጹሑ ላይ መማለጃን የማይቀበል። እንዲህ የሚያደርግ ለዘለዓለም አይታወክም።


ገዥዎችሽ ዐመፀኞችና የሌባ ግብረ ዐበሮች ናቸው፤ ሁሉም ጉቦን ይወዳሉ፤ እጅ መንሻንም በብርቱ ይፈልጋሉ፤ አባት ለሌላቸው አይቆሙም፤ የመበለቶችንም አቤቱታ አይሰሙም።


የወይን ጠጅ ለመጠጣት ጀግኖች፤ የሚያሰክር መጠጥ ለመደባለቅ ብርቱ ለሆኑ ወዮላቸው!


በጽድቅ የሚሄድ ቅን ነገርንም የሚናገር፥ በጭቆና የሚገኝ ትርፍን የሚጸየፍ፥ መማለጃን ከመጨበጥ እጁን የሚሰበስብ፥ ደም ማፍሰስን ከመስማት ጆሮቹን የሚከልል፥ ክፋትንም ከማየት ዐይኖቹን የሚጨፍን ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios