Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 18:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ይህንም ብታደርግና፥ እግዚአብሔር ቢያዝዝህ፥ መቋቋም ትችላለህ፥ ደግሞም ይህ ሕዝብ ሁሉ በሰላም ወደ ስፍራው በሰላም ይሄዳል።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 አንተ ይህን ብታደርግና እግዚአብሔርም ይህንኑ ቢያዝዝህ፣ ድካምህን መቋቋም ትችላለህ፤ እነዚህም ሰዎች ሁሉ ረክተው ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 በዚህ ዐይነት ብትሠራና ይህም የእግዚአብሔር ፈቃድ ቢሆን ራስህን በከንቱ አታደክምም፤ ሕዝቡም በቀላሉ ጉዳዩ እየተፈጸመለት ወደየቤቱ ይሄዳል።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ይህ​ንም ቃሌን ብታ​ደ​ርግ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያበ​ረ​ታ​ሃል፤ መፍ​ረ​ድም ትች​ላ​ለህ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ በሰ​ላም ወደ ስፍ​ራው ይመ​ለ​ሳል።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ይህንም ብታደርግ፥ እግዚአብሔር እንዲሁ ቢያዝዝህ፥ መቆም ይቻልሃል፥ ደግሞም ይህ ሕዝብ ሁሉ በሰላም ወደ ስፍራው ይደርሳል።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 18:23
15 Referencias Cruzadas  

አንተ ከአንተም ጋር ያለው ሕዝብ ትደክማላችሁ፤ ይህ ነገር ይከብድሃልና፤ አንተ ብቻህን ልታደርገው አትችልም።


ጌታም፥ “አድምጣቸው፤ ንጉሥም አንግሥላቸው” አለው። ከዚያም ሳሙኤል የእስራኤልን ሰዎች፥ “እያንዳንዳችሁ ወደ ከተማችሁ ተመለሱ” አላቸው።


ሰዎቹ ግን፥ “አንተ መውጣት የለብህም፤ እንድንሸሽ ብንገደድ፥ ስለኛ ምንም አይገዳቸውም፤ ግማሾቻችን እንኳ ብንሞት፥ ስለኛ ምንም አይገዳቸውም፤ አንተ ግን ብቻህን ከእኛ ከዐሥሩ ሺህ ትበልጣለህ! ስለዚህ በከተማ ሆነህ ብትረዳን ይሻላል” አሉት።


እግዚአብሔርም ከአብርሃም ጋር ንግግሩን በጨረሰ ጊዜ ሄደ፥ አብርሃምም ወደ ስፍራው ተመለሰ።


እንደ ተገለጠልኝም ወጣሁ፤ ምናልባትም በከንቱ እንዳልሮጥ ወይም ሮጬ እንዳልሆን፥ በአሕዛብ መካከል የምሰብከውን ወንጌል፥ በመሪነታቸው ለታወቁት ለብቻቸው አስታወቅኋቸው።


በእነርሱና በጳውሎስ በበርናባስም መካከል ብዙ ጥልና ክርክር በሆነ ጊዜ፥ ስለዚህ ክርክር ጳውሎና በርናባስ ከእነርሱም አንዳንዶች ሌሎች ሰዎች ወደ ሐዋርያት ወደ ሽማግሌዎችም ወደ ኢየሩሳሌም ይወጡ ዘንድ ተቆረጠ።


የጽሩያ ልጅ አቢሳ ግን ዳዊትን ለመታደግ መጣ፤ ፍልስጥኤማዊውንም መትቶ ገደለው። ከዚያም የዳዊት ሰዎች፥ “የእስራኤል መብራት እንዳይጠፋ ከእንግዲህ አንተ ከእኛ ጋር ወደ ጦርነት መውጣት የለብህም” ብለው ማሉለት።


ንጉሡም፥ “ኪምሃም ከእኔ ጋር ይሻገራል፤ አንተን ደስ የሚያሰኝህንም ሁሉ አደርግለታለሁ፤ ከእኔ የምትፈልገውን ማናቸውንም ነገር ለአንተም አደርግልሃለሁ” አለው።


ራሔልም ዮሴፍን ከወለደች በኋላ ያዕቆብ ላባን እንዲህ አለው፦ “ወደ ስፍራዬ ወደ አገሬም እመለስ ዘንድ አሰናብተኝ።


ጌታ ሰንበትን እንደ ሰጣችሁ እዩ፤ ስለዚህ በስድስተኛው ቀን የሁለት ቀን ምግብ ሰጣችሁ፤ ሰው ሁሉ በስፍራው ይቀመጥ፤ በሰባተኛው ቀን ማንም ከስፍራው አይውጣ።”


በሕዝቡ ላይ ሁልጊዜ ይፍረዱ፤ ትልቁን ነገር ሁሉ ወደ አንተ ያምጡት፥ ትንሹንም ነገር ሁሉ እነርሱ ይፍረዱ፤ እነርሱም ከአንተ ጋር ሸክሙን ይሸከማሉ፥ ለአንተም ይቀልልሃል።


ሙሴም የአማቱን ቃል ሰማ፥ ያለውንም ሁሉ አደረገ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios