Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤፌሶን 6:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ባርያም ሆነ ነጻ ሰው፥ እያንዳንዱ ለሚያደርገው መልካም ነገር ሁሉ ከጌታ ብድራቱን እንደሚቀበል ታውቃላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ምክንያቱም ባሪያም ሆነ ነጻ ሰው ለሚያደርገው በጎ ነገር ሁሉ ሽልማቱን ከጌታ እንደሚቀበል ታውቃላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ባሪያም ሆነ ጌታ እያንዳንዱ በሠራው መልካም ሥራ ከጌታ ዋጋውን የሚቀበል መሆኑን ታውቃላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ጌታም ቢሆን፥ አገ​ል​ጋ​ይም ቢሆን መል​ካም ያደ​ረገ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ዋጋ እን​ደ​ሚ​ያ​ገኝ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ባሪያ ቢሆን ወይም ጨዋ ሰው፥ እያንዳንዱ የሚያደርገውን መልካም ነገር ሁሉ ከጌታ በብድራት እንዲቀበለው ታውቃላችሁና።

Ver Capítulo Copiar




ኤፌሶን 6:8
20 Referencias Cruzadas  

ይህንንም ስታደርጉ ከጌታ የርስትን ሽልማት እንደምትቀበሉ ታውቃላችሁና፤ የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስን ነው።


የሚመልሱት አጸፋ የላቸውምና ብፁዕ ትሆናለህ፤ በጻድቃን ትንሣኤ ይመለስልሃልና።”


በዚህም መታደስ ግሪካዊና አይሁዳዊ፥ የተገረዘና ያልተገረዘ፥ አረማዊና እስኩቴስ፥ ባርያና ነጻ ሰው የሚባል ነገር አይኖርም፤ ነገር ግን ክርስቶስ ሁሉ ነው፤ በሁሉም ነው።


መልካም ሆነ ወይም ክፉ፥ በሥጋችን እንደ ሠራነው ዋጋችንን ለመቀበል፥ ሁላችን በክርስቶስ የፍርድ ዙፋን ፊት እንቆማለን።


የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣልና፤ በዚያን ጊዜ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ይከፍለዋል።


ይህም ምጽዋትህ በስውር እንዲሆን ነው። በስውር የሚያይ አባትህ ይከፍልሃል።


ክፉ ሰው የሐሰት ደመወዝ ያገኛል፥ ጽድቅን የሚዘራ ግን የታመነ ዋጋ አለው።


ስለዚህ ታላቅ ዋጋ ያለውን መታመናችሁን አትጣሉ።


በእውነት መጨረሻህ ያምራልና፥ ተስፋህም አይጠፋምና።


ወደ ፊት የሚቀበለውን ብድራት ከሩቅ ተመልክቶአልና፥ ከግብጽ ሀብት ይልቅ ስለ ክርስቶስ መነቀፍ እጅግ የሚበልጥ ሀብት መሆኑን ተገነዘበ።


በክርስቶስ ኢየሱስ ሁላችሁም አንድ ናችሁና አይሁዳዊ ወይም ግሪካዊ የለም፥ ባርያ ወይም ነጻ ሰው የለም፥ ወንድ ወይም ሴት የለም።


“ሰዎች እንዲያዩላችሁ ብላችሁ መልካምም ሥራችሁን በፊታቸው እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ፤ አለበለዚያ በሰማያት ካለው አባታችሁ ዘንድ ሽልማት አታገኙም።


ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና።”


በደለኞች ወዮላቸው፤ ጥፋት ይመጣባቸዋል፤


ነገር ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ መልካምም አድርጉ፤ ይመለስልናልም ብላችሁ ምንም ተስፋ ሳታደርጉ አበድሩ፤ ዋጋችሁም ታላቅ ይሆናል፤ የልዑልም ልጆች ትሆናላችሁ፤ እርሱ ለማያመሰግኑና ለክፉዎች ቸር ነውና።


አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባርያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል።


የሚበድልም እንደ በደሉ መጠን ብድራቱን ይቀበላል፤ ለሰው ፊትም አድልዎ የለምና።


እነርሱም ‘የሚቀጥረን ስለ አጣን ነው፤’ አሉት። እርሱም ‘እናንተም ወደ ወይኔ አትክልት ቦታ ሂዱ፤’ አላቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios