Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤፌሶን 5:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 እንዲሁም ጉድፍ ወይም የፊት መጨማደድ ወይም አንዳች እንከን ሳይገኝባት ቅድስትና ነውር የሌለባት አድርጎ ክብርት የሆነችን ቤተ ክርስቲያንን ለራሱ ሊያቀርባ እንደፈለገ፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 እንዲሁም ጕድፍ ወይም የፊት መጨማደድ ወይም አንዳች እንከን ሳይገኝባት ቅድስትና እንከን አልባ የሆነች ክብርት ቤተ ክርስቲያን አድርጎ ለራሱ ሊያቀርባት ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 በዚህ ዐይነት ዕድፍ ወይም የፊት መጨማደድ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ መጥፎ ነገር ሳይገኝባት ቅድስት፥ እንከን የሌለባትና ውብ አድርጎ ወደራሱ ያቀርባታል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 የነ​ጻ​ችና የተ​ቀ​ደ​ሰች ትሆን ዘንድ እንጂ በላ​ይዋ እድ​ፈት ወይም ርኵ​ሰት እን​ዳ​ያ​ገ​ኝ​ባት፥ ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ኑን ለእ​ርሱ የከ​በ​ረች ያደ​ር​ጋት ዘንድ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 እድፈት ወይም የፊት መጨማደድ ወይም እንዲህ ያለ ነገር ሳይሆንባት ቅድስትና ያለ ነውር ትሆን ዘንድ ክብርት የሆነችን ቤተ ክርስቲያን ለራሱ እንዲያቀርብ ፈለገ።

Ver Capítulo Copiar




ኤፌሶን 5:27
21 Referencias Cruzadas  

አሁን በእርሱ ፊት ያለ ነውርና ያለ ነቀፋ ቅዱሳን አድርጎ ለማቅረብ በሥጋዊው አካሉ በሞቱ አስታረቃችሁ።


ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበው የክርስቶስ ደም እንዴት ልቆ፥ ሕያው እግዚአብሔርን ለማምለክ፥ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን!


ነገር ግን ነውርና እድፍ እንደሌለው በግ ደም፥ በክርስቶስ ክቡር ደም ነው፥


ዓለም ሳይፈጠር፥ በፍቅር በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን እድንሆን በክርስቶስ መረጠን።


እንደ አንዲት ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ለማቅረብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፥ በእግዚአብሔር ቅንዐት እቀናላችኋለሁና።


እኛም በክርስቶስ ፍጹም አድርገን ሁሉንም ሰው ለማቅረብ ሁሉንም ሰው እየገሠጽንና ሁሉንም ሰው በጥበብ ሁሉ እያስተማርን የምንሰብከው እርሱ ነው፤


ምክንያቱም ጌታን ኢየሱስን ያስነሣው እኛንም ከኢየሱስ ጋር እንደሚያስነሣንና ከእናንተም ጋር በፊቱ እንደሚያቀርበን እናውቃለን።


ወዳጄ ሆይ፥ ሁለንተናሽ ውብ ነው፥ ነውርም የለብሽም።


አሁንም ሳትሰናከሉ ሊጠብቃችሁ፥ በክብሩ ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ ሊያቆማችሁ ለሚችለው፤


ስለዚህ ወዳጆች ሆይ! ይህን ሁሉ እየተጠባበቃችሁ፥ ጌታ ያለ ነውር ወይም ያለ ነቀፋ ሆናችሁ በሰላም እንዲያገኛችሁ በትጋት ኑሩ፤


ወደ ዘለዓለም ሕይወት የሚያደርሰውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ ሳለ፥ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ።


የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ መንፈሳችሁም ነፍሳችሁም ሥጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ።


የጢሮስ ሴት ልጅ፥ የምድር ባለ ጠጎች አሕዛብ በፊትሽ ደጅ ይጠናሉ።


የምሠራላቸውንም በጎነት ሁሉ በሚሰሙ የምድር አሕዛብ ሁሉ ፊት ይህች ከተማ ለእኔ የምስጋናና የክብር የደስታም ስም ትሆናለች፤ እኔም ስላደረግሁላት በጎነትና ሰላም ሁሉ ይፈራሉ ይንቀጠቀጣሉም።


በጌታ እጅ የውበት አክሊል፥ በአምላክሽም እጅ የመንግሥት ዘውድ ትሆኛለሽ።


የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ፥ ስለ አንቺ የተከበረ ነገር ይባላል።


እነዚህ ከሴቶች ጋር ያልረከሱ ናቸው፤ ድንግሎች ናቸውና። በጉ ወደሚሄድበትም የሚከተሉት እነዚህ ናቸው። ለእግዚአብሔርና ለበጉ በኵራት እንዲሆኑ ከሰዎች የተዋጁ እነዚህ ናቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios