Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መክብብ 3:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ያም እድል ፈንታው ነውና ሰው በሥራው ደስ ከሚሰኝበት ነገር በቀር ሌላ መልካም ነገር እንደሌለው አየሁ፥ ከእርሱ በኋላስ የሚሆነውንስ ወስዶ ማን ያሳየዋል?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ስለዚህ ለሰው ዕጣ ፈንታው ስለ ሆነ፣ በሥራው ከመደሰት የተሻለ ነገር እንደሌለው አየሁ፤ ከርሱ በኋላ የሚሆነውንስ ተመልሶ እንዲያይ የሚያደርገው ማን ነው?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 የሰው ዕድል ፈንታ ይኸው ስለ ሆነ በሚሠራው ነገር ደስ ከሚለው በቀር ሌላ የሚያደርገው ምንም ነገር እንደሌለ አስተዋልኩ፤ ከሞተም በኋላ የሚሆነውን ነገር የሚያውቅ ማንም የለም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ያም ዕድል ፋን​ታው ነውና ሰው በሥ​ራው ደስ ከሚ​ለው በቀር ሌላ መል​ካም ነገር እን​ደ​ሌ​ለው አየሁ፤ ከእ​ርሱ በኋ​ላስ የሚ​ሆ​ነ​ውን ያይ ዘንድ የሚ​ያ​መ​ጣው ማን ነው?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ያም እድል ፈንታው ነውና ሰው በሥራው ደስ ከሚለው በቀር ሌላ መልካም ነገር እንደሌለው አየሁ፥ ከእርሱ በኋላስ የሚሆነውን ያይ ዘንድ የሚያመጣው ማን ነው?

Ver Capítulo Copiar




መክብብ 3:22
24 Referencias Cruzadas  

ልጆቹ ቢከብሩ አያውቅም፥ ቢዋረዱም አያይም።


ሰነፍ ቃሉን ያበዛል፥ ሰው ግን የሚሆነውን አያውቅም፥ ከእርሱስ በኋላ የሚሆነውን ማን ይነግረዋል?


አንተ ጐበዝ፥ በጉብዝናህ ደስ ይበልህ፥ በጉብዝናህም ወራት ልብህን ደስ ይበለው፥ በልብህም መንገድ ዐይኖችህም በሚያዩት ሂድ፥ ዳሩ ግን ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንዲያመጣህ እወቅ።


ከእኔ በኋላ ለሚመጣው ሰው እተወዋለሁና ከፀሐይ በታች የደከምሁበትን ሁሉ ጠላሁት።


ለሰው በመብላትና በመጠጣት፥ እንዲሁም በመጣር ከሚያገኘው ደስታ የሚሻለው ነገር የለም፥ ይህም ደግሞ ከእግዚአብሔር እጅ እንደተሰጠ አየሁ።


ሰው በከንቱ የሕይወቱ ቀናት ቍጥር ና እንደ ጥላ በሚያሳልፈው ዘመኑ በሕይወቱ ሳለ ለሰው የሚሻለውን የሚያውቅ ማነው? ወይስ ከፀሐይ በታች ከእርሱ በኋላ የሚሆነውን ለሰው ማን ይነግረዋል?


በመልካም ቀን ደስ ይበልህ፥ በክፉም ቀን ተመልከት፥ ሰው ከእርሱ በኋላ መርምሮ ምንም እንዳያገኝ እግዚአብሔር ይህንንም ያንንም እንዲሁ ሠርቶአል።


ከመብላትና ከመጠጣት፥ ደስም ከመሰኘት በቀር ለሰው ልጅ ከፀሐይ በታች ሌላ ምንም መልካም ነገር የለውምና እኔ ደስታን አመሰገንሁ፥ ይህም እግዚአብሔር ከፀሐይም በታች በሰጠው በሕይወቱ ዘመን በድካሙ ከእርሱ ጋር ይኖራል።


የሚሆነውንም አያውቅም፥ እንዴትስ እንደሚሆን የሚነግረው ማን ነው?


ሰውም ጊዜውን አያውቅም፥ በክፉ መረብ እንደ ተጠመዱ ዓሣዎች፥ በወጥመድም እንደ ተያዙ ወፎች፥ እንዲሁ የሰው ልጆች በክፉ ጊዜ በድንገት ሲወድቅባቸው ይጠመዳሉ።


ፍቅራቸውና ጥላቸው ቅንዓታቸውም በአንድነት ከወዲሁ ጠፍቶአል፥ ከፀሐይ በታችም በሚሠራው ነገር ለዘለዓለም እድል ፈንታ ከእንግዲህ ወዲህ የላቸውም።


“ስለዚህ ስለነገ አትጨነቁ፥ ነገ ስለ ራሱ ይጨነቃልና፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።


አምላክህ ጌታ በሚመርጠው ስፍራ አንተ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ፥ ወንድና ሴት አገልጋዮችህ፤ በከተሞችህ የሚኖር ሌዋዊም፥ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ትበሉታላችሁ፤ እጅህም በነካው ነገር ሁሉ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይልሃል።


በዚያም በጌታ በአምላካችሁ ፊት ትበላላችሁ፤ ጌታ አምላካችሁ እናንተን በባረከበት፥ በምታደርጉት ሁሉ አንተና ቤተሰቦችህ ሐሤት ታደርጋላችሁ።”


ሁሉን አብዝቶ ስለ ሰጠህ ጌታ እግዚአብሔርን በልቡና ደስታና ሐሤት አላገለገልኸውምና፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos