Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 8:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እርሱን በመፍራትና የእርሱንም መንገድ በመከተል፥ የጌታ የአምላክህን ትእዛዞች ጠብቅ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 በመንገዶቹ በመሄድና እርሱንም በማክበር፣ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ጠብቅ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እርሱን በመፍራትና የእርሱንም መንገድ በመከተል፥ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ሁሉ ጠብቅ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በመ​ን​ገ​ዱም እን​ድ​ት​ሄድ፥ እር​ሱ​ንም እን​ድ​ት​ፈራ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ጠብቅ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በመንገዱም እንድትሄድ እርሱንም እንድትፈራ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ጠብቅ።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 8:6
9 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ ለአባቶቻችን በሰጠኸው ምድር ላይ በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ ይፍሩህ በመንገዶችህም ይሂዱ።


የመዓርግ መዝሙር። ጌታን የሚፈሩት ሁሉ፥ በመንገዶቹም የሚሄዱ ምስጉኖች ናቸው።


ሥርዓቱንና ሕጉን አስተምራቸው፥ የሚሄዱበትን መንገድና የሚያደርጉትን ሥራ አሳውቃቸው።


ሁለቱም በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ፤ በጌታ ትእዛዛትና ሕግጋት ሁሉ ያለ ነቀፋ ይመላለሱ ነበር።


እኔንም ለመፍራት ሁልጊዜም ትእዛዜን ሁሉ ለመጠበቅ፥ እንዲህ ያለ ልብ ምነው ሁልግዜ በኖራቸው! ለእነርሱ ለልጆቻቸውም ለዘለዓለም መልካም በሆነላቸው ነበር!


በሕይወት እንድትኖሩ፥ መልካምም እንዲሆንላችሁ፥ በምትወርሱአትም ምድር ዕድሜአችሁ እንዲረዝም፥ ጌታ አምላካችሁ ባዘዛችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ።


እንግዲህ ሰው ልጁን እንደሚገሥፅ፥ እንዲሁም ጌታ እግዚአብሔር አንተን እንደሚገሥጽህ በልብህ አስተውል።


ጌታ አምላክህ ወደ መልካም ምድር፥ ከሸለቆና ከኮረብታ የሚመነጩ የውኃ ጅረቶችና ፈሳሾች፥ ምንጮችም ወዳሉባት ምድር፥


ብቻ ጌታን ፍሩ፤ በፍጹም ልባችሁ በታማኝነት አምልኩት፤ ያደረገላችሁንም ታላላቅ ነገሮች አስቡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos