Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 4:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በጌታ በአምላካችሁ ፊት በኮሬብ በቆማችሁበት ቀን፥ ጌታ፦ ‘ሕዝቡን ወደ እኔ ሰብስብ፥ በምድርም በሕይወት በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ እኔን መፍራት እንዲማሩ፥ ልጆቻቸውንም እንዲያስተምሩ፥ ቃሌን አሰማቸዋለሁ’ ብሎ በተናገረኝ ጊዜ፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 “በምድሪቱ በሚኖሩበት ጊዜ ሁሉ እኔን ማክበር እንዲማሩ፣ ለልጆቻቸውም እንዲያስተምሩ ቃሌን ይሰሙ ዘንድ ሕዝቡን በፊቴ ሰብስብ” ባለኝ ጊዜ፣ በኮሬብ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት የቆማችሁበትን ዕለት አስታውሱ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እግዚአብሔር ‘ቃሌን ይሰሙ ዘንድ ስለምፈልግ ሕዝቡን ሰብስብ’ ባለኝ ጊዜ በሲና ተራራ ላይ በእግዚአብሔር ፊት በቆማችሁበት ቀን ‘በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ ለእኔ እንዲታዘዙና፥ ልጆቻቸውም እኔን መፍራትን ያውቁ ዘንድ ያስተምሩአቸው’ ያለውን አስታውሱ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን ወደ እኔ ሰብ​ስ​ባ​ቸው፤ እነ​ርሱ በም​ድር ላይ በሕ​ይ​ወት በሚ​ኖ​ሩ​በት ዘመን ሁሉ እኔን መፍ​ራት ይማ​ሩና ለል​ጆ​ቻ​ቸ​ውም ያስ​ተ​ምሩ ዘንድ ቃሌን ይስሙ ብሎ​ኛ​ልና በኮ​ሬብ በተ​ሰ​በ​ሰ​ባ​ችሁ ጊዜ በፈ​ጣ​ሪ​ያ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እንደ ቆማ​ችሁ ንገ​ራ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 4:10
25 Referencias Cruzadas  

ጌታም ሙሴን፦ “ከአንተ ጋር ስነጋገር ሕዝቡ እንዲሰሙና ለዘለዓለም እንዲያምኑህ፥ እነሆ በከባድ ደመና እመጣለሁ” አለው። ሙሴም የሕዝቡን ቃል ለጌታ ነገረ።


አምላኩን ጌታን ማክበር ይማር ዘንድ፥ የዚህን ሕግ ቃል ሁሉና ይህን ሥርዓት በጥንቃቄ እንዲከተል ከእርሱ ጋር ይሁን፤ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ያንብበው፤


ጌታ አምላካችን በኮሬብ ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ።


ሙሴም ለሕዝቡ እንዲህ አላቸው፦ “አትፍሩ ሊፈትናችሁ፥ ኃጢአትንም እንዳትሠሩ እርሱን መፍራት በልባችሁ እንዲሆን እግዚአብሔር መጥቷልና።”


ሕዝቡም ሁሉ ነጎድጓዱንና መብረቁን፥ የቀንደ መለከቱን ድምፅ፥ ተራራውንም ሲጤስ አዩ፤ ሕዝቡም ፈሩ ተንቀጠቀጡም፥ ርቀውም ቆሙ።


እንዲህም ሆነ በሦስተኛው ቀን ማለዳ ነጎድጓድ፥ መብረቅና ከባድ ደመና እጅግም የበረታ የቀንደ መለከት ድምጽ በተራራው ላይ ሆነ፤ በሰፈሩ የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተንቀጠቀጡ።


የነገሩን ሁሉ ፍጻሜ እንስማ፥ ይህ የሰው ሁለንተናው ነውና፥ እግዚአብሔርን ፍራ፥ ትእዛዙንም ጠብቅ።


ድምፅም ከዙፋኑ እንዲህ ሲል ወጣ፦ “ባርያዎቹ ሁሉ እርሱንም የምትፈሩት ታናናሾችና ታላላቆች ሆይ! አምላካችንን አመስግኑ፤”


የሚናገረው እምቢ እንዳትሉ ተጠንቀቁ፤ እነዚያ በምድር ላይ ሲያስረዳቸው እምቢ ያሉት ካላመለጡ፥ ከሰማይ የመጣው ሲያስጠነቅቀን ፈቀቅ የምንል እኛ እንዴት እናመልጣለን?


ምሕረቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ በሚፈሩት ላይ ይኖራል።


ብቻ ጌታን ፍሩ፤ በፍጹም ልባችሁ በታማኝነት አምልኩት፤ ያደረገላችሁንም ታላላቅ ነገሮች አስቡ።


ምንጊዜም ጌታ እግዚአብሔርን ማክበር ትማር ዘንድ፥ የወይን ጠጅና የዘይትህን አሥራት፥ የቀንድ ከብትህን፥ የበግና የፍየል መንጋህን በኵራት ስሙ እንዲጠራበት በሚመርጠው ስፍራ፥ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ትበላለህ።


እኔንም ለመፍራት ሁልጊዜም ትእዛዜን ሁሉ ለመጠበቅ፥ እንዲህ ያለ ልብ ምነው ሁልግዜ በኖራቸው! ለእነርሱ ለልጆቻቸውም ለዘለዓለም መልካም በሆነላቸው ነበር!


የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ምድር በወጡ በሦስተኛው ወር በዚያ ቀን ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ።


“ብቻ አስተውል፥ ነፍስህንም በትጋት ጠብቅ፤ ዐይኖችህ ያዩትን ነገር እንዳትረሳ፥ በሕይወትህም ዘመን ሁሉ ከልብህ እንዳይለይ፥ ለልጆችህም ለልጅ ልጆችህም አሳውቃቸው።


ልጆቻችሁንም አስተምሯቸው፤ ቤት ስትቀመጥ፥ መንገድ ስትሄድ፥ ስትተኛና ስትነሣ ስለዚህ አጫውታቸው።


“የአባቶቻችሁ አምላክ ጌታ፥ እንድትወርሷት በሰጣችሁ ምድር ላይ በምትኖሩበት ጊዜ ሁሉ፥ በጥንቃቄ ልትከተሏቸው የሚገባችሁ ሥርዓቶችና ሕጎች እነዚህ ናቸው።


ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤቱን እንዲያዝዝ አውቃለሁና፥” ይህም እግዚአብሔር በአብርሃም ላይ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያመጣ ዘንድ ነው።


በሦስተኛውም ቀን ይዘጋጁ፤ በሦስተኛው ቀን ሕዝቡ ሁሉ እያዩ ጌታ በሲና ተራራ ላይ ይወርዳልና።


አንተ ልጅህም የልጅ ልጅህም፥ በምትኖርበት ዘመን ሁሉ፤ ጌታ አምላክህን ፈርተህ እኔ ለአንተ ያዘዝሁትን፥ ሥርዓቱንና ትእዛዙን ሁሉ በመጠበቅ፥ ዕድሜህም ይረዝም ዘንድ፤


ለልጆችህም አስተምረው፥ በቤትህም ስትቀመጥ፥ በመንገድም ስትሄድ፥ ስትተኛም ሆነ፥ ስትነሣም ንገራቸው።


ትውልደ ትውልድ ሥራህን ያመሰግናሉ፥ ኃይልህንም ያወራሉ።


እኔ ዛሬ እንደማደርግ ሕያዋን እነርሱ ያመሰግኑሃል፤ አባት ለልጆቹ እውነትህን ያስታውቃል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios