ዘዳግም 31:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 ዮርዳኖስን ተሻግረህ በምትወርሷት ምድር በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ ይህን ሕግ የማያውቁት ልጆቻቸውም መስማትና ጌታ አምላካችሁንም መፍራት ሊማሩ ይገባቸዋል።” Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 ዮርዳኖስን ተሻግረህ በምትወርሷት ምድር፣ በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ፣ ይህን ሕግ የማያውቁት ልጆቻቸውም መስማትና አምላካችሁን እግዚአብሔርን መፍራት ሊማሩ ይገባቸዋል።” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 በዚህም ዐይነት የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ሕግ ሰምተው የማያውቁ ዘሮቻችሁ ሁሉ ሊያዳምጡት ይችላሉ፤ ስለዚህም ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሱአት ምድር በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ ለእግዚአብሔር መታዘዝን ይማራሉ።” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 የማያውቁ ልጆቻቸውም ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ልትወርሱአት በምትሄዱባት ምድር በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ ይስሙ፤ አምላካችሁን እግዚአብሔርንም መፍራት ይማሩ።” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 የሕግን ቃላት የማያውቁ ልጆቻቸውም ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ልትወርሱአት በምትሄዱባት ምድር በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ ይስሙ፥ አምላካችሁን እግዚአብሔርንም መፍራት ይማሩ። Ver Capítulo |