Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 29:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ሰዎችም እንዲህ ይላሉ፦ ‘የአባቶቻቸው አምላክ ጌታ ከግብጽ ምድር ባወጣቸው ጊዜ ከእነርሱ ጋር የገባውን ኪዳን ትተዉ፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 መልሱም፣ “የአባቶቻቸው አምላክ እግዚአብሔር ከግብጽ ምድር ባወጣቸው ጊዜ፣ ከእነርሱ ጋራ የገባውን ኪዳን ሕዝቡ ስለ ተዉ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 መልሱም፦ ‘እነርሱ የቀድሞ አባቶቻቸው አምላክ ከግብጽ ምድር ባወጣቸው ጊዜ ከእነርሱ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን በማፍረሳቸው ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ሰዎ​ችም እን​ዲህ ይላሉ፦ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ብፅ ምድር ባወ​ጣ​ቸው ጊዜ ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር ያደ​ረ​ገ​ውን ቃል ኪዳን ስለ​ተዉ፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ሰዎችም እንዲህ ይላሉ፦ የአባቶቻቸው አምላክ እግዚአብሔር ከግብፅ ምድር ባወጣቸው ጊዜ ከእነርሱ ጋር ያደረገውን ቃል ኪዳን ስለተዉ፥

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 29:25
20 Referencias Cruzadas  

ይህ ከፍ ከፍ ብሎ የሚታየው ቤተ መቅደስ ፈርሶ የፍርስራሽ ክምር ይሆናል፤ በዚያ በኩል የሚያልፉ ሰዎች ይህን አይተው በመደንገጥ ‘እግዚአብሔር ይህን አገርና ይህን ቤተ መቅደስ ለምን እንዲህ አደረገ?’ በማለት ይሳለቁበታል።


ራሳቸው የሚሰጡትም መልስ ‘የእስራኤል ሕዝብ የቀድሞ አባቶቻቸውን ከግብጽ ምድር ያወጣ ጌታ አምላካቸውን በመተዋቸው ምክንያት ነው፤ ከዚህም በቀር ለእግዚአብሔር የነበራቸውን ታማኝነት ትተው ሌሎችን አማልክት አመለኩ፤ ሰገዱላቸውም፤ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ የጥፋት መቅሠፍት ያመጣባቸውም ስለዚህ ነው’ የሚል ነው።”


የሰጣቸውንም ድንጋጌ አልተቀበሉም፤ ከቀድሞ አባቶቻቸው ጋር የገባውንም ቃል ኪዳን አልጠበቁም፤ የሰጣቸውንም ማስጠንቀቂያዎች ሁሉ ቸል አሉ፤ ለከንቱ ጣዖቶች በመስገድ ራሳቸውም ከንቱዎች ሆኑ፤ የእነርሱን መጥፎ ምሳሌነት እንዳይወርሱ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ትእዛዝ በመሻር በዙሪያቸው የሚኖሩ የአሕዛብን ልማድ ሁሉ ተከተሉ።


እስራኤላውያን አምላካቸው እግዚአብሔር የሚጠላውን ነገር ሁሉ አደረጉ፤ ከዘብ ጠባቂዎች ማማ አንሥቶ እስከ ትልቅ ከተማ ድረስ በገጠር ከተሞቻቸው ሁሉ በየኰረብታዎቹ የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎችን ሠሩ፤


እነርሱ እኔን ትተው ለባዕዳን አማልክት መሥዋዕት አቅርበዋል፤ በእጃቸው በሠሩአቸው ጣዖቶች ሁሉ እኔን አስቆጥተውኛል፤ ቁጣዬም አይበርድም፤


ደግሞም በጌታ አምሎት በነበረው በንጉሡ በናቡከደናፆር ላይ ዓመፀ፤ ወደ እስራኤልም አምላክ ወደ ጌታ እንዳይመለስ አንገቱን አደነደነ ልቡንም አጠነከረ።


ለጣዖቶቻቸውም ተገዙ፥ ወጥመድም ሆኑባቸው።


በሕዝቤ ላይ ተቈጥቼ ነበር፤ ርስቴንም አረከስሁ፤ በእጅሽም አሳልፌ ሰጠኋቸው፤ ከእነርሱ ጋር ምሕረት አላደረግሽም፤ በሽማግሌዎቻቸው ላይ ቀንበርሽን እጅግ አክብደሻል።


እናንተን ጌታን የተዋችሁትን ግን፥ ቅዱሱንም ተራራዬን የረሳችሁትን፥ ዕጣ ፋንታ ለተባለ ጣዖትም ማዕድ ያዘጋጃችሁትን፥ ዕድል ለተባለ ጣዖትም የወይን ጠጅ ለመጠጥ ቁርባን የቀዳችሁትን፥


አንተም እንዲህ ትላቸዋለህ፦ ‘አባቶቻችሁ እኔን ስለ ተው ነው፥ ይላል ጌታ፥ ሌሎችንም አማልክት ተከተሉ አገለገሉአቸውም ሰገዱላቸውም፥ እነርሱም ትተውኛል፥ ሕጌንም አልጠበቁም፤


ብዙ አሕዛብም በዚህች ከተማ አጠገብ ያልፋሉ፥ ሁሉም ባልንጀሮቻቸውን፦ ጌታ በዚህች ታላቅ ከተማ ለምን እንዲህ አደርገ?” ይላሉ።


እነርሱም፦ “የአምላካቸውን የጌታን ቃል ኪዳን ትተው ለሌሎች አማልክት ስለ ሰገዱ ስላገለገሉአቸውም ነዋ ብለው ይመልሳሉ።”


እጃቸውን ይዤ ከግብጽ አገር ባወጣኋቸው ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደ አደረግሁት ያለ ቃል ኪዳን አይደለም፤ እኔ ገዢአቸው ብሆንም እንኳ ያን ያደረግሁትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል፥ ይላል ጌታ።


ይህም የሆነው ስለ ሠሩት ክፋት እኔን ስላስቈጡኝ፥ በዚህም እናንተም አባቶቻችሁም እነርሱም ለማያውቁአቸው ለሌሎች አማልክት ለማጠንና ለማገልገል ስለ ሄዱ ነው።


ያገኙአቸው ሁሉ አጠፉአቸው፥ ጠላቶቻቸውም፦ በጽድቅ ማደሪያ በጌታ ላይ፥ በአባቶቻቸው ተስፋ በጌታ ላይ እነርሱ ኃጢአት ስለ ሠሩ እኛ አልበደልንም፥ አሉ።


ወጥተውም የማያውቋቸውን፥ እርሱም ያላዘዛቸውን ሌሎችን አማልክት አመለኩ፤ ሰገዱላቸውም።


ከግብጽ ምድር ለማውጣት እጃቸውን በያዝሁበት ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደገባሁት ኪዳን አይደለም፤ እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና እኔም ቸል አልኳቸው፤ ይላል ጌታ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos