Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 15:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ከመንጋህ፥ ከአውድማህና ከወይን መጭመቂያህ በልግስና ስጠው፤ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ባረከህ መጠን ትሰጠዋለህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ከመንጋህ፣ ከዐውድማህና ከወይን መጭመቂያህ በልግስና ስጠው፤ አምላክህ እግዚአብሔር በባረከህ መጠን ስጠው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እግዚአብሔር አምላክህ ከሰጠህ በረከት፥ ማለት፥ ከበጎች፥ ከእህልና ከወይን በልግሥና ስጠው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ነገር ግን ከበ​ጎ​ችህ፥ ከእ​ህ​ል​ህም፥ ከወ​ይ​ን​ህም መጭ​መ​ቂያ ስንቅ ትሰ​ን​ቅ​ለ​ታ​ለህ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ባረ​ከህ መጠን ትሰ​ጠ​ዋ​ለህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ነገር ግን ከመንጋህ፥ ከአውድማህም፥ ከወይንህም መጥመቂያ ትለግስለታለህ፤ አምላክህ እግዚአብሔር እንደ ባረከህ መጠን ትሰጠዋለህ።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 15:14
8 Referencias Cruzadas  

እኔ በምመጣበት ጊዜ የገንዘብ መዋጮ እንዳይደረግ፤ ከእናንተ እያንዳንዱ እንደገቢው መጠን በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን እየለየ ያስቀምጥ፤


እንዲሁ እየደከማችሁ ድውዮችን ልትረዱና እርሱ ራሱ ‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው፤’ እንዳለ የጌታን የኢየሱስን ቃል ልታስቡ ይገባችሁ ዘንድ በሁሉ አሳየኋችሁ።”


የጌታ በረከት ሀብታም ታደርጋለች፥ ኀዘንንም ከእርሷ ጋር አይጨምርም።


አቤቱ፥ የተትረፈረፈ ዝናብ ለርስትህ አዘነብህ፥ በደከመም ጊዜ አንተ አጸናኸው።


እርሱም፦ “ሂዱ፥ የሰባውን ብሉ፥ ጣፋጩንም ጠጡ፥ ለእነዚያ ምንም ላልተዘጋጀላቸው ድርሻቸውን ላኩ፤ ይህ ቀን ለጌታችን ቅዱስ ነውና፤ አትዘኑ የጌታ ደስታ ኃይላችሁ ነውና” አላቸው።


ነጻ በምታወጣው ጊዜ ባዶ እጁን አትስደደው።


አንተም ራስህ በግብጽ ባርያ እንደ ነበርክና ጌታ እግዚአብሔር እንደ ተቤዠህ አስታውስ፤ ስለዚህ እኔ ዛሬ ይህን ነገር አዝሃለሁ።


በተነ፥ ለችግረኞችም ሰጠ፥ ጽድቁ ለዘለዓለም ዓለም ይኖራል፥ ቀንዱም በክብር ከፍ ከፍ ይላል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios