አሞጽ 9:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 ጌታን በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ አየሁት፤ እርሱም እንዲህ አለ፦ መድረኮቹ እስኪናወጡ ድረስ ጉልላቶቹን ምታ፥ በሰዎቹም ራስ ሁሉ ላይ ሰባብራቸው፤ እኔም ከእነርሱ የቀሩትን በሰይፍ እገድላለሁ፤ የሚሸሽ አያመልጥም፥ የሚያመልጥም አይድንም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 ጌታን በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ አየሁት፤ እርሱም እንዲህ አለ፤ “መድረኮቹ እንዲናወጡ፣ ጕልላቶቹን ምታ፤ በሕዝቡም ሁሉ ራስ ላይ ሰባብራቸው፤ የቀሩትን በሰይፍ እገድላቸዋለሁ፤ ከእነርሱ አንድም ሰው አይሸሽም፤ ቢሸሽም የሚያመልጥ የለም። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 እግዚአብሔርን በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ አየሁት፤ እርሱም እንዲህ ሲል አዘዘ፦ “መድረኮቹ እስኪናወጡ ድረስ የቤተ መቅደሱን ጒልላት ምታ፤ ሰባብረህም በሰዎቹ አናት ላይ እንዲደረመስ አድርግ፤ ከዚያ የተረፉትንም እኔ በሰይፍ እጨርሳቸዋለሁ፤ ማንም መሸሽ አይችልም፤ ማንም ሊያመልጥ አይችልም። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 እግዚአብሔርን በመሠውያው ላይ ቆሞ አየሁት፤ እርሱም እንዲህ አለኝ፥ “አበቦች የተሳሉባቸውን ምሰሶዎችን ምታ፤ መድረኮቹም ይናወጣሉ፤ ራሳቸውንም ቍረጥ፤ እኔም ከእነርሱ የቀሩትን በሰይፍ እገድላለሁ፤ ከሚሸሹትም የሚያመልጥ የለም፤ ከሚያመልጡትም የሚድን የለም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 ጌታን በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ አየሁት፥ እርሱም እንዲህ አለ፦ መድረኮቹ ይናወጡ ዘንድ ጕልላቶቹን ምታ፥ በራሳቸውም ሁሉ ላይ ሰባብራቸው፥ እኔም ከእነርሱ የቀሩትን በሰይፍ እገድላለሁ፥ የሚሸሽ አያመልጥም፥ የሚያመልጥም አይድንም። Ver Capítulo |