ሐዋርያት ሥራ 7:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)31-32 ሙሴም አይቶ ባየው ተደነቀ፤ ሊመለከትም ሲቀርብ የጌታ ቃል ‘እኔ የአባቶችህ አምላክ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ፤’ ብሎ ወደ እርሱ መጣ። ሙሴም ተንቀጥቅጦ ሊመለከት አልደፈረም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም31 ሙሴም ባየው ነገር ተደነቀ፤ ነገሩን ለማጣራት ወደዚያ ሲቀርብ የጌታ ድምፅ፤ Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም31 ሙሴ ይህን ባየ ጊዜ ተገረመ፤ ቀረብ ብሎም ሲመለከት እንዲህ የሚለውን የጌታ ድምፅ ሰማ፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)31 ሙሴም አይቶ በአየው ተደነቀ፤ ሊያስተውለውም ቀረበ፤ እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ተናገረው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)31-32 ሙሴም አይቶ ባየው ተደነቀ፤ ሊመለከትም ሲቀርብ የጌታ ቃል፦ ‘እኔ የአባቶችህ አምላክ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ’ ብሎ ወደ እርሱ መጣ። ሙሴም ተንቀጥቅጦ ሊመለከት አልደፈረም። Ver Capítulo |