Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 20:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 እኔ ከሄድኩ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ እንደ ተኲላ ጨካኞች የሆኑ ሰዎች እንደሚገቡባችሁ ዐውቃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 እኔ ከሄድሁ በኋላ፣ ነጣቂ ተኵላዎች መጥተው በመካከላችሁ ሠርገው እንደሚገቡና ለመንጋውም እንደማይራሩ ዐውቃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 እኔ ከሄድኩ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ እንደ ተኲላ ጨካኞች የሆኑ ሰዎች እንደሚገቡባችሁ ዐውቃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ከእኔ በኋላ ለመ​ን​ጋ​ዪቱ የማ​ይ​ራሩ ነጣ​ቂ​ዎች ተኵ​ላ​ዎች እን​ደ​ሚ​መጡ እኔ አው​ቃ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29-30 ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 20:29
18 Referencias Cruzadas  

“ዓይናችሁን አንሥታችሁ እነዚህን ከሰሜን የሚመጡትን ተመልከቱ፤ ለአንቺ የተሰጠ መንጋ፥ የተዋበ መንጋሽ፥ ወዴት አለ?


“የማሰማርያዬን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው!” ይላል ጌታ።


በውስጧ ያሉ አለቆችዋ የገደሉትን እንደሚቦጫጭቁ ተኩላዎች ናቸው። ተገቢ ያልሆነ ትርፍ ለማግኘት ሲሉ ደምን ያፈስሳሉ፥ ነፍሶችንም ያጠፋሉ።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔም ሕያው ነኝና እረኛ ስለ ሌለ እረኞቼም በጎቼን ስላልፈለጉ እረኞችም ራሳቸውን እንጂ በጎቼን ስላላሰማሩ፥ በጎቼ ንጥቂያ ሆነዋልና፥ በጎቼም ለምድር አራዊት ሁሉ መብል ሆነዋልና


በውስጧ የሚኖሩ ባለ ሥልጣኖቿ የሚያገሡ አንበሶች ናቸው፥ ፈራጆችዋም ለጠዋት ምንም የማያስቀሩ የማታ ተኩላዎች ናቸው።


መንጋውን ለሚተው ለማይረባ እረኛ ወዮለት! ሰይፍ ክንዱንና ቀኝ ዓይኑን ይውጋው፤ ክንዱም ፈጽማ ትሰልስል፤ ቀኝ ዓይኑም ፈጽማ ትታወር።


“እነሆ እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ብልሆች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።


“የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ፥ በውስጣቸው ነጣቂ ተኩላዎች ናቸው።


እንግዲህ ሂዱ፤ እነሆ፥ እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ።


“አንተ ታናሽ መንጋ! መንግሥትን ሊሰጣችሁ የአባታችሁ በጎ ፈቃድ ነውና አትፍሩ።


እረኛ ያልሆነው በጎቹም የእርሱ ያልሆኑት ተቀጣሪው ግን፥ ተኩላ ሲመጣ ባየ ጊዜ በጎቹን ትቶ ይሸሻል፤ ተኩላም ይነጥቃቸዋል፤ በጎቹንም ይበትናቸዋል።


ከበሉ በኋላም ኢየሱስ ስምዖን ጴጥሮስን “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! ከእነዚህ ይበልጥ ትወደኛለህን?” አለው። “አዎን ጌታ ሆይ! እንደምወድህ አንተ ታውቃለህ፤” አለው። ኢየሱስም “ግልገሎቼን አሰማራ፤” አለው።


በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።


ኀላፊነት የተሰጣችሁን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ ይህም በግድ ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ፍላጎት በፈቃደኝነት፥ ለጥቅም በመስገብገብ ሳይሆን በጽኑ ፍላጎት ይሁን፤


ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል እንደ ነበሩ፤ እንዲሁም በመካከላችሁ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይኖራሉ፤ እነርሱም ጥፋትን የሚያስከትሉ ትምህርቶች አስርገው በማስገባት የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው፥ በራሳቸው ላይ ፈጣን ጥፋትን ያመጣሉ።


እነርሱ “በመጨረሻው ዘመን ክፉ ምኞታቸውን የሚከተሉ ተሳላቂዎች ይሆናሉ፤” ብለዋችኋልና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos