Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 15:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 አያሌ ቀንም ከተቀመጡ በኋላ ከወንድሞች በሰላም ተሰናብተው ወደ ሐዋርያት ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 በዚያም ጥቂት ጊዜ ከቈዩ በኋላ፣ ከወንድሞች በሰላም ተሰናብተው ወደ ላኳቸው ሰዎች ተመለሱ። [

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ይሁዳና ሲላስ ጥቂት ቀኖች እዚያ ከቈዩ በኋላ ከአማኞች ወንድሞች ጋር ተሰነባብተው ወደ ላኩአቸው ተመልሰው ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 በእ​ነ​ር​ሱም ዘንድ አያሌ ቀን ከተ​ቀ​መጡ በኋላ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን ተሰ​ና​ብ​ተው በሰ​ላም ወደ ሐዋ​ር​ያት ተመ​ለሱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 አያሌ ቀንም ከተቀመጡ በኋላ ከወንድሞች በሰላም ተሰናብተው ወደ ሐዋርያት ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 15:33
9 Referencias Cruzadas  

እኛ አንተን እንዳልነካንህ፥ በጎነትንም ብቻ እንዳሳየንህ፥ በሰላምም እንደ ሰደድንህ፥ አንተም ክፉ እንዳትሠራብን፥ አንተ አሁንም ከጌታ ዘንድ የተባረክህ ነህ።”


ሙሴም ሄደ፥ ወደ አማቱ ወደ ይትሮ ተመለሰ፥ እርሱም፦ “እባክህን በግብጽ ወዳሉ ዘመዶቼ እንድመለስ እስካሁንም በሕይወት እንዳሉ ሄጄ እንዳይ ፍቀድልኝ” አለው። ይትሮም ሙሴን፦ “በሰላም ሂድ” አለው።


እርሱም፥ “ልጄ ሆይ፥ እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ፤ ከሥቃይሽም ተፈወሺ” አላት።


ያንጊዜ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ከቤተ ክርስቲያኑ ሁሉ ጋር ከእነርሱ የተመረጡትን ሰዎች ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋር ወደ አንጾኪያ ይልኩ ዘንድ ፈቀዱ፤ እነርሱም በወንድሞች መካከል ዋናዎች ሆነው በርስያን የተባለው ይሁዳና ሲላስ ነበሩ።


ሲላስ ግን በዚያ ይኖር ዘንድ ፈቀደ።


የወኅኒውም ጠባቂ “ትፈቱ ዘንድ ገዢዎቹ ልከዋል፤ እንግዲህ አሁን ወጥታችሁ በሰላም ሂዱ፤” ብሎ ይህን ቃል ለጳውሎስ ነገረው።


ስለዚህ ማንም አይናቀው፤ በሰላም ወደ እኔ እንዲመለስ እርዱት፤ መመለሱንም ከወንድሞች ጋር እየጠበቅን ነው።


ጋለሞታይቱ ረዓብ ሰላዮችን በሰላም ስለ ተቀበለቻቸው በእምነቷ ምክንያት ከማይታዘዙ ጋር አልጠፋችም።


ማንም ወደ እናንተ ቢመጣ ይህንም ትምህርት ባያመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት፤ ሰላምም አትበሉት፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos