Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ሳሙኤል 10:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ኢዮአብም እንዲህ አለ “ሶርያውያን የሚያይሉብኝ ከሆነ አንተ መጥተህ ትረዳኛለህ፤ አሞናውያን የሚያይሉብህ ከሆነ ደግሞ እኔ መጥቼ እረዳሃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ኢዮአብም እንዲህ አለ፤ “ሶርያውያን ከበረቱብኝ አንተ መጥተህ ትረዳኛለህ፤ አሞናውያን ከበረቱብህ ደግሞ እኔ መጥቼ እረዳሃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ኢዮአብም አቢሳይን እንዲህ አለው “ሶርያውያን ድል ሊያደርጉኝ መቃረባቸውን በምታይበት ጊዜ መጥተህ እርዳኝ፤ እኔም ዐሞናውያን አንተን ድል ሊያደርጉህ በሚቃረቡበት ጊዜ መጥቼ እረዳሃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እር​ሱም አለው፥ “ሶር​ያ​ው​ያን ቢበ​ረ​ቱ​ብኝ ትረ​ዳ​ኛ​ለህ፤ የአ​ሞን ልጆ​ችም ቢበ​ረ​ቱ​ብህ እኔ መጥቼ እረ​ዳ​ሃ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ሶርያውያን ቢበረቱብኝ ትረዳኛለህ፥ የአሞን ልጆች ቢበረቱብህ እኔ መጥቼ እረዳሃለሁ።

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 10:11
8 Referencias Cruzadas  

የእርስ በርሳችሁን ሸክም ተሸከሙ፥ በዚህም የክርስቶስን ሕግ ትፈጽማላችሁ።


እኛ ብርቱዎች የሆንን የደካሞችን ድካም መሸከም እንጂ ራሳችንን ማስደሰት የለብንም።


እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ ጸለይሁ፤ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና፤” አለ።


የቀሩትን ሰዎች ደግሞ በወንድሙ በአቢሳ ሥር መድቦ በአሞናውያን ግንባር አሰለፋቸው።


እንግዲህ በርታ፤ ለሕዝባችንና ለአምላካችን ከተሞች በጀግንነት እንዋጋ፤ ጌታም በፊቱ መልካም መስሎ የታየውን ያድርግ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios