2 ቆሮንቶስ 9:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ነገር ግን ለእነርሱ እንደተናገርኩት፥ ስለ እናንተ ያለን ትምክህት እንዲሁ በባዶ እንዳልሆነ ለማረጋገጥ ወንድሞችን እልካለሁ፤ Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 እንግዲህ በዚህ ነገር በእናንተ ላይ ያለን ትምክሕት ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር፣ አስቀድሞ ስለ እናንተ እንደ ተናገርሁት ተዘጋጅታችሁ እንድትገኙ ወንድሞችን ልኬአለሁ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 በዚህ ነገር በእናንተ ላይ ያለን ትምክሕት ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር እነዚህን ወንድሞች እልካለሁ፤ እናንተም ልክ እኔ ከዚህ በፊት እንዳልኩት ተዘጋጅታችሁ ጠብቁ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 በዚህም ያመሰገንናችሁ ምስጋና በእነርሱ ዘንድ ሐሰት እንዳይሆንብን፥ እንደ ነገርናቸውም ተዘጋጅታችሁ እንዲያገኙአችሁ ወንድሞችን ወደ እናንተ ላክናቸው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 ነገር ግን ለእነርሱ እንዳልሁ፥ የተዘጋጃችሁ ትሆኑ ዘንድ በዚህም ነገር ስለ እናንተ ያለው ትምክህታችን ከንቱ እንዳይሆን ወንድሞችን እልካለሁ፤ Ver Capítulo |