Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 6:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 አንተ በማደሪያህ በሰማይ ሆነህ ስማ፤ የምድርም አሕዛብ ሁሉ ስምህን እንዲያውቁ፥ እንደ ሕዝብህም እንደ እስራኤል እንዲፈሩህ፥ ይህም የሠራሁት ቤት በስምህ እንደ ተጠራ እንዲያውቁ፥ እንግዳው የሚለምንህን ሁሉ አድርግ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 አንተ በማደሪያህ በሰማይ ሆነህ ስማ፤ የምድር ሕዝቦች ሁሉ እንደ ገዛ ሕዝብህ እንደ እስራኤል፣ ስምህን በማወቅ እንዲፈሩህ፣ የሠራሁትም ይህ ቤት ስምህ የሚጠራበት ቤት መሆኑን እንዲያውቁ ባዕዱ ሰው የሚጠይቅህን ሁሉ አድርግ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 አንተ ጸሎቱን ስማ፤ ሕዝብህ እስራኤል እንደሚያደርገው በመላው ዓለም የሚኖሩ ሕዝቦች አንተን በማወቅ ታዛዦች እንዲሆኑልህ፥ በምትኖርበት በሰማይ ሆነህ የዚህን ሰው ጸሎት ስማ፤ እንድታደርግለት የሚለምንህን ሁሉ ፈጽምለት፤ ይህም በሚሆንበት ጊዜ ይህ እኔ የሠራሁት ቤተ መቅደስ የአንተ ስም የሚጠራበት ስፍራ መሆኑን ያውቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 አንተ በማ​ደ​ሪ​ያህ በሰ​ማይ ስማ፤ የም​ድ​ርም አሕ​ዛብ ሁሉ ስም​ህን ያውቁ ዘንድ፥ እንደ ሕዝ​ብ​ህም እንደ እስ​ራ​ኤል ይፈ​ሩህ ዘንድ፥ በዚ​ህም በሠ​ራ​ሁት ቤት ስምህ እንደ ተጠራ ያውቁ ዘንድ፥ እን​ግ​ዳው የሚ​ለ​ም​ን​ህን ሁሉ አድ​ርግ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 አንተ በማደሪያህ በሰማይ ስማ፤ የምድርም አሕዛብ ሁሉ ስምህን ያውቁ ዘንድ፥ እንደ ሕዝብህም እንደ እስራኤል ይፈሩህ ዘንድ፥ በዚህም በሠራሁት ቤት ስምህ እንደ ተጠራ ያውቁ ዘንድ፥ እንግዳው የሚለምንህን ሁሉ አድርግ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 6:33
16 Referencias Cruzadas  

‘ሕዝቤን እስራኤልን ከግብጽ ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ፥ ስሜ የሚጠራበት ቤተ መቅደስ የሚሠራበት በመላው እስራኤል ምንም ዓይነት ከተማ አልመረጥኩም፤ አሁን ግን በሕዝቤም በእስራኤል ላይ ይነግሥ ዘንድ ዳዊትን መርጫለሁ።’


እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ አንተ ብቻ አምላክ መሆንህን የዓለም መንግሥታት ሁሉ ያውቁ ዘንድ አሁን ከአሦር ንጉሥ በመታደግ አድነን።”


“ሕዝብህም ጠላቶቻቸውን ለመውጋት አንተ በምትልካቸው መንገድ ቢወጡ፥ አንተም ወደ መረጥሃት ወደዚህች ከተማ እኔም ለስምህ ወደ ሠራሁት ቤት ለአንተ ቢጸልዩ፥


በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ራሳቸውን አዋርደው ቢጸልዩ፥ ፊቴንም ቢፈልጉ፥ ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱ፥ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ፥ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ።


ችግረኞች ይበላሉ፥ ይጠግቡማል፥ ጌታንም የሚሹት ያመሰግኑታል፥ ልባቸውም ለዘለዓለም ሕያው ይሁን።


እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ጦርነትን ያስቆማል፥ ቀስትን ይሰብራል፥ ጦርንም ይቆራርጣል፥ በእሳትም ጋሻን ያቃጥላል።


እግዚአብሔር ይማረን ይባርከንም፥ ፊቱንም በላያችን ያብራ፥


ያደረግሃቸው አሕዛብ ሁሉ ይመጣሉ፥ አቤቱ፥ በፊትህም ይሰግዳሉ፥ ስምህንም ያከብራሉ፥


በዚያን ቀን፤ የእሴይ ሥር ለሕዝቦች ምልክት ሆኖ ይቆማል፤ መንግሥታት ወደ እርሱ ይመጣሉ፤ ማረፊያውም የከበረ ይሆናል።


እርሱም፦ “የያዕቆብን ነገዶች እንድታስነሣ ከእስራኤልም የተረፉትን እንድትመልስ አገልጋዬ እንድትሆን እጅግ ቀላል ነገር ነውና ማዳኔ እስከ ምድር ዳር እንዲደርስ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌ ሰጥቼሃለሁ ይላል።


የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ! በአሕዛብ ጥበበኞች ሁሉ መካከል በመንግሥታቸውም ሁሉ እንደ አንተ ያለ ስለ ሌለ፥ አንተን መፍራት ይገባልና አንተን የማይፈራ ማን ነው?


እነርሱም ስሜን በእስራኤል ልጆች ላይ ያኖራሉ፤ እኔም እባርካቸዋለሁ።”


ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በሰማይም እንዲህ የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ተሰሙ፦ “የዓለም መንግሥት የጌታችንና የመሢሑ ሆነች፤ ለዘለዓለምም እስከ ዘለዓለም ይነግሣል፤”


ጌታ ዛሬ አንተን በእጄ አሳልፎ ይሰጣል፤ እኔ መትቼ እጥልሃለሁ፤ ራስህንም እቆርጠዋለሁ። በዚህች ዕለት የፍልስጥኤማውያንን ሠራዊት ሬሣ ለሰማይ አሞሮችና ለምድር አራዊት እሰጣለሁ፤ ዓለምም ሁሉ በእስራኤል ዘንድ እግዚአብሔር መኖሩን ያውቃል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos