Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 6:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ከእስራኤልም ልጆች ጋር ያደረገው የጌታ ቃል ኪዳን ያለበትን ታቦት በዚያው ውስጥ አኖርሁ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 በዚያም እግዚአብሔር ከእስራኤል ሕዝብ ጋራ የገባው ኪዳን ያለበትን ታቦት አኑሬአለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እግዚአብሔር ከእስራኤል ሕዝብ ጋር የገባው ቃል ኪዳን ያለበትን ታቦትም በቤተ መቅደሱ ውስጥ አኑሬአለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ከሕ​ዝ​ቡም ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ያደ​ረ​ገው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ኪዳን ያለ​ባ​ትን ታቦት በዚ​ያው ውስጥ አኖ​ርሁ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ከእስራኤልም ልጆች ጋር ያደረገው የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ያለበትን ታቦት በዚያው ውስጥ አኖርሁ።”

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 6:11
9 Referencias Cruzadas  

በታቦቱም ውስጥ የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ፥ ጌታም ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን ባደረገ ጊዜ ሙሴ በኮሬብ ካስቀመጣቸው ከሁለቱ ጽላቶች በቀር ምንም አልነበረበትም።


ካህናቱም የጌታን ቃል ኪዳን ታቦት ወደ ቤቱ አምጥተው በመቅደሱ በውስጠኛው ክፍል በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ከኪሩቤል ክንፍ በታች በነበረው በስፍራው አኖሩት።


በዚያም ውስጥ የወርቅ ማዕጠንት ነበር፤ ሁለንተናዋም በወርቅ የተለበጠች የኪዳን ታቦት፥ በእርስዋም ውስጥ መና ያለባት የወርቅ መሶብና የበቀለች የአሮን በትር የኪዳኑም ጽላት ነበሩ።


ከግብጽ ምድር ባወጣቸው ጊዜ ከቀድሞ አባቶቻችን ጋር ጌታ ያደረገው ቃል ኪዳን ላለበት ታቦት ማኖሪያ አዘጋጅቼአለሁ።”


የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር እንደ ወጡ፥ ጌታ ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን በገባ ጊዜ፥ ሙሴ በኮሬብ ተራራ በቃል ኪዳኑ ታቦት ውስጥ ካኖራቸው ከሁለቱ የድንጋይ ጽላቶች በቀር ሌላ ምንም ነገር አልነበረም።


ጽላቱን ወስዶ በታቦቱ ውስጥ አኖረው፥ መሎጊያዎቹንም በታቦቱ አደረገ፥ የስርየት መክደኛውንም በታቦቱ ላይ አኖረው፤


ጌታም የተናገረውን ቃል ፈጸመ፤ ጌታም ተስፋ እንደሰጠ በአባቴ በዳዊት ፋንታ ተነሣሁ፥ በእስራኤልም ዙፋን ላይ ተቀመጥሁ፥ ለእስራኤልም አምላክ ለጌታ ስም ቤት ሠራሁ።


ሰሎሞንም የእስራኤል ጉባኤ ሁሉ እያዩት በጌታ መሠዊያ ፊት ቆሞ እጆቹን ዘረጋ፤


“ከእኔ ጋር በመሥዋዕት ኪዳን ያቆሙትን ቅዱሳኑን ሰብስቡልኝ” ይላል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios