2 ዜና መዋዕል 35:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 ይህም ፋሲካ ኢዮስያስ በነገሠ በዓሥራ ስምንተኛው ዓመት ተከበረ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 ይህ ፋሲካ የተከበረው በኢዮስያስ ዘመነ መንግሥት በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት ነበር። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 ይህም በዓል የተከበረው፥ ኢዮስያስ በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት ነበር። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 ይህም ፋሲካ ኢዮስያስ በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት ተደረገ። 19 ‘ሀ’ ንጉሡ ኢዮስያስ ካህኑ ኬልቅያስ በእግዚአብሔር ቤት ባገኘው መጽሐፍ የተጻፉትን ቃላት ሁሉ ለመጠበቅ አስማተኞችንና ጠንቋዮችን፥ ሟርተኞችንና በኢየሩሳሌም ምድርና በይሁዳ የሚገኙትን ምስሎችና ቃሪያሲም የተባሉ ጣዖታትን በእሳት አቃጠለ። 19 ‘ለ’ እንደ ሙሴ ሕግ ሁሉ በፍጹም ልቡ፥ በፍጹም ነፍሱ፥ በፍጹም ኀይሉ ከእርሱ በፊት ከነበሩት ወደ እግዚአብሔር የተመለሰ የሚመስለው ሰው አልነበረም። ከእርሱም በኋላ የሚመስለው አልተነሣም። 19 ‘ሐ’ ነገር ግን እግዚአብሔር ንጉሥ ምናሴ በይሁዳ ላይ በአደረገውና በአነሣሣው ጥፋት ሁሉ ከአስከተለው ታላቅ ቍጣ አልተመለሰም። 19 ‘መ’ እግዚአብሔርም አለ፥ “እስራኤልን እንዳራቅሁ ይሁዳን ከፊቴ አርቃለሁ። የመረጥኋትንም ከተማ ኢየሩሳሌምንና ስሜ በዚያ ይጠራበታል ያልሁትን ቤት እጥላለሁ።” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 ይህም ፋሲካ ኢዮስያስ በነገሠ በአሥራ ስምንተኛው ዓመት ተደረገ። Ver Capítulo |