Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 32:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ነገር ግን የባቢሎን መሳፍንት መልእክተኞች በአገሩ ላይ ስለተደረገው ተአምራት ለመጠየቅ ወደ እርሱ በተላኩ ጊዜ ጌታ እርሱን ለመፈተንና በልቡ ያለውን ሁሉ ለማወቅ ሲል ተወው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ነገር ግን በምድሪቱ ላይ ስለ ተፈጸመው ታምራዊ ምልክት እንዲጠይቁት፣ የባቢሎን ገዦች መልእክተኞችን በላኩ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ሊፈትነውና በልቡ ያለውን ሁሉ ሊያውቅ ስለ ፈለገ ተወው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ነገር ግን የባቢሎን መልእክተኞች በአገሪቱ ስለ ተደረገው አስደናቂ ነገር ሊጠይቁት ወደ እርሱ መጥተው በነበረ ጊዜ እግዚአብሔር በሕዝቅያስ ልብ ውስጥ ያለውን ሐሳብ ለማወቅ ይፈትነው ዘንድ ተወው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ነገር ግን የባ​ቢ​ሎን መሳ​ፍ​ንት መል​እ​ክ​ተ​ኞች በሀ​ገሩ ላይ ስለ ተደ​ረ​ገው ተአ​ም​ራት ይጠ​ይ​ቁት ዘንድ ወደ እርሱ በተ​ላኩ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ት​ነ​ውና በልቡ ያለ​ውን ሁሉ ያውቅ ዘንድ ተወው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ነገር ግን የባቢሎን መሳፍንት መልእክተኞች በአገሩ ላይ ስለ ተደረገው ተአምራት ይጠይቁት ዘንድ ወደ እርሱ በተላኩ ጊዜ እግዚአብሔር ይፈትነውና በልቡ ያለውን ሁሉ ያውቅ ዘንድ ተወው።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 32:31
24 Referencias Cruzadas  

ከእነዚህም ነገሮች በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው፥ “አብርሃም!” ብሎ ጠራው፤ አብርሃምም፥ “እነሆ፥ አለሁኝ!” ብሎ መለሰ።


በዚያም ወራት ሕዝቅያስ እስኪሞት ድረስ ታመመ፥ ወደ ጌታም ጸለየ፤ እርሱም ተናገረው፥ ምልክትም ሰጠው።


ሕዝቅያስ ግን እንደ ተቀበለው ቸርነት መጠን አላደረገም፥ ልቡም ኰራ፤ ስለዚህም በእርሱና በይሁዳ በኢየሩሳሌምም ላይ ቁጣ ሆነ።


የሕዝቅያስም የቀረው ነገር፥ ቸርነቱም፥ እነሆ፥ በአሞጽ ልጅ በነቢዩ በኢሳይያስ ራእይ በይሁዳና በእስራኤልም ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፎአል።


ፊትህን ከእኔ አትሰውር፥ ተቈጥተህ ከባርያህ ፈቀቅ አትበል፥ ረዳት ሁነኝ፥ አትጣለኝም፥ የመድኃኒቴም አምላክ ሆይ፥ አትተወኝ።


ማቅለጫ ለብር፥ ከውር ለወርቅ ነው፥ ጌታ ግን ልብን ይፈትናል።


አንድ ሦስተኛውን ክፍል ወደ እሳት አስገባለሁ፤ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፤ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፤ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፤ እኔም፦ “ይህ ሕዝቤ ነው” እላለሁ፥ እርሱም፦ “ጌታ አምላኬ ነው” ይላል።


እኔ የወይን ግንድ ነኝ፤ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና፤ በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።


አምላካችሁን ጌታ በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ ትወዱት እንደሆነ ያውቅ ዘንድ አምላካችሁ ጌታ ሊፈትናችሁ ነውና፥ የዚያን ነቢይ ቃል ወይም ሕልም አላሚውን አትስሙ።


በመጨረሻም መልካም ነገር ሊያደርግልህ፥ ሊፈትንህ ሊያዋርድህም አባቶችህ ያላወቁትን መና በምድረ በዳ ያበላህን፥


ጌታ አምላክህ ሊያስጨንቅህ፥ ትእዛዙን ትጠብቅ ወይም አትጠብቅ እንደሆነ፥ በልብህ ያለውን ያውቅ ዘንድ ሊፈትንህ፥ በእነዚህ በአርባ ዓመታት በምድረ በዳ የመራህን መንገድ ሁሉ አስታውስ።


ማንም ሲፈተን “እግዚአብሔር ፈተነኝ፤” አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈተንምና፤ እርሱስ ማንንም አይፈትንም።


በዚህም በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ ነው።


እርሷም፥ “ሳምሶን፤ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” አለችው። ሳምሶን ከእንቅልፉ ነቅቶ፥ “እንደ ወትሮው አደርጋለሁ” አለ፤ ነገር ግን ጌታ እንደ ተወው አላወቀም ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos