Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 3:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 የኪሩቤልም ክንፎች ሀያ ክንድ ሙሉ ተዘርግተው ነበር፤ የአንዱ ኪሩብ ክንፍ አምስት ክንድ ነበረ፥ የቤቱንም ግንብ ይነካ ነበረ፤ ሁለተኛው ክንፍ አምስት ክንድ ነበረ፥ የሁለተኛውንም ኪሩብ ክንፍ ይነካ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ከዳር እስከ ዳር ገጥሞ የተዘረጋው የኪሩቤል ክንፍ በጠቅላላው ሃያ ክንድ ነበር፤ የመጀመሪያው ኪሩብ አንዱ ክንፍ ዐምስት ክንድ ሆኖ የቤተ መቅደሱን ግድግዳ ሲነካ፣ ሌላው ዐምስት ክንድ የሆነው ክንፉ ደግሞ የሁለተኛውን ኪሩብ ክንፍ ይነካ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11-13 ኪሩቤል በቅድስተ ቅዱሳን መግቢያ ትይዩ ጐን ለጐን ቆመው ነበር፤ እያንዳንዱ ኪሩብም ሁለት ክንፎች ነበሩት፤ የእያንዳንዱም ክንፍ ርዝመት ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር ነበር፤ ሁለቱ ክንፎች በየአቅጣጫው የተዘረጉ ሆነው በክፍሉ መኻል ላይ እርስ በርሳቸው ይነካካሉ፤ ሌሎቹ ሁለቱ ክንፎቻቸው ደግሞ እያንዳንዱ በየአቅጣጫው ያለውን ግድግዳ የሚነካ ሲሆን፥ የእነዚህ የተዘረጉ ክንፎች ጠቅላላ ወርድ ዘጠኝ ሜትር ያኽል ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የኪ​ሩ​ቤ​ልም ክን​ፎች ሃያ ክንድ ሙሉ ተዘ​ር​ግ​ተው ነበር፤ የአ​ንዱ የኪ​ሩብ ክንፍ ርዝ​መት አም​ስት ክንድ ነበረ፤ የቤ​ቱ​ንም ግንብ ይነካ ነበር፤ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ክንፍ ርዝ​መት አም​ስት ክንድ ነበረ፤ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ው​ንም ኪሩብ ክንፍ ይነካ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 የኪሩቤልም ክንፎች ሃያ ክንድ ሙሉ ተዘርግተው ነበር፤ የአንዱ ኪሩብ ክንፍ አምስት ክንድ ነበረ፤ የቤቱንም ግንብ ይነካ ነበረ፤ ሁለተኛው ክንፍ አምስት ክንድ ነበረ፤

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 3:11
4 Referencias Cruzadas  

ኪሩቤልንም በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ እንዲቆሙ አደረገ፤ ስለዚህም የተዘረጉ ሁለቱ ክንፎቻቸው በክፍሉ መካከለኛ ቦታ ላይ ተገናኝተው ሌሎቹ ሁለቱ ክንፎቻቸው ደግሞ በተዘረጉበት አቅጣጫ ግንቦቹን ይነኩ ነበር።


በቅድስተ ቅዱሳንም ውስጥ ከእንጨት ሥራ ሁለቱን ኪሩቤል ሠራ፥ በወርቅም ለበጣቸው።


የሁለተኛውም ኪሩብ ክንፍ አምስት ክንድ ነበረ፥ የቤቱንም ግንብ ይነካ ነበረ፤ ሁለተኛውም ክንፍ አምስት ክንድ ነበረ የሌላውንም ኪሩብ ክንፍ ይነካ ነበረ።


ክንፎቻቸው እርስ በእርሱ ይነካካ ነበር፥ ሲሄዱም አይዞሩም፥ እያንዳንዱም ቀጥ ብሎ ይሄድ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos