Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 29:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 አባቶቻችን ተላልፈዋል፥ በአምላካችንም በጌታ ፊት ክፉ አድርገዋል፤ እርሱንም ትተዋል፥ ፊታቸውንም ከጌታ መኖሪያ መልሰዋል፥ ወደ እርሷም ጀርባቸውን አዙረዋል፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 አባቶቻችን ታማኞች አልነበሩም፣ በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ ተዉትም። ከእግዚአብሔር ማደሪያ ፊታቸውን መለሱ፤ ጀርባቸውንም አዞሩበት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 የቀድሞ አባቶቻችን ለአምላካችን ለእግዚአብሔር የነበራቸውን ታማኝነት አጓድለዋል፤ እርሱንም በመተው የእርሱ መኖሪያ ከሆነው ስፍራ ፊታቸውን አዞሩ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 አባ​ቶ​ቻ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርቀ​ዋል፤ በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አድ​ር​ገ​ዋል፤ እር​ሱ​ንም ረስ​ተ​ዋል፤ ፊታ​ቸ​ው​ንም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መል​ሰ​ዋል፤ ጀር​ባ​ቸ​ው​ንም አዙ​ረ​ዋል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 አባቶቻችን ተላልፈዋል፤ በአምላካችንም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አድርገዋል፤ እርሱንም ትተዋል፤ ፊታቸውንም ከእግዚአብሔር መኖሪያ መልሰዋል፤

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 29:6
21 Referencias Cruzadas  

“በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን ሁሉ ለማድረግ አባቶቻችን የጌታን ቃል ስላልጠበቁ፥ በእኛ ላይ የነደደው የጌታ ቁጣ እጅግ ታላቅ ነውና ሄዳችሁ ስለ ተገኘው የመጽሐፍ ቃል ለእኔ በእስራኤልና በይሁዳም ለቀሩት ጌታን ጠይቁ።”


ነገር ግን አባቶቻችን የሰማያትን አምላክ ስላስቆጡት በከለዳዊው በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፥ እርሱም ይህን ቤት አፈረሰ፥ ሕዝቡንም ወደ ባቢሎን አፈለሰ።


ከአባቶቻችን ዘመን ጀምረን እስከ ዛሬ ድረስ በታላቅ በደል ነበርን፤ ዛሬም እንደ ሆነው ስለ ኃጢአታችን እኛ፥ ነገሥታቶችንና ካህናቶቻችን ለሰይፍ፥ ለምርኮ፥ ለብዝበዛና ለእፍረት በምድር ነገሥታት እጅ ተሰጠን።


እኔ አገልጋይህ ዛሬ በፊትህ ስለ አገልጋዮችህ ስለ እስራኤል ልጆች ሌሊትና ቀን የምጸልየውን ጸሎት ለመስማት ጆሮህ ያድምጥ፥ ዐይኖችህም ይከፈቱ፥ በአንተ ላይ ያደረግነውን የእስራኤልን ልጆች ኃጢአት እናዘዛለሁ፤ እኔና የአባቴ ቤት ኃጢአት አድርገናል።


“እነርሱና አባቶቻችን ግን ታበዩ፥ አንገታቸውን አደነደኑ፥ ትእዛዞችህንም አልሰሙም፤


“አሁንም አምላካችን ሆይ፥ ቃል ኪዳንና ምሕረትን የምትጠብቅ ታላቅና ኃያል የተፈራኸውም አምላክ ሆይ፥ ከአሦር ነገሥታት ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በእኛና በነገሥታቶቻችን በአለቆቻችንም በካህናቶቻችንም በነብዮቻችንም በአባቶቻችንም በሕዝብህ ሁሉ ላይ የደረሰው መከራ ሁሉ በፊትህ ጥቂት መስሎ አይታይህ።


ነገሥታቶቻችንም አለቆቻችንም ካህናቶቻችንም አባቶቻችንም ሕግህን አልጠበቁም፥ የመሰከርህባቸውንም ትእዛዝህንና ምስክርህን አልሰሙህም።


አቤቱ! ኃይሌ፥ አምባዬ፥ በመከራም ቀን መጠጊያዬ፥ ከምድር ዳርቻ አሕዛብ ወደ አንተ መጥተው እንዲህ ይላሉ፦ “በእውነት አባቶቻችን ውሸትንና ከንቱን ነገር የማይረባቸውንም ወርሰዋል፤


ሕዝቤ ሁለት ክፉ ነገሮችን ሠርቷል፤ እኔን የሕይወት ውኃ ምንጭን ትተውኛል፥ ውኃ መቋጠር የማይችሉ የተሸነቈሩ ጉድጓዶች ለራሳቸው ቆፍረዋል።


በመንገድ በመራሽ ጊዜ ጌታ አምላክሽን በመተው በራስሽ ላይ ይህን አላመጣሽምን?


ግንዱን፦ ‘አንተ አባቴ ነህ፤’ ድንጋዩንም፦ ‘አንቺ ወለድሺኝ’ ይላሉ፤ ፊታቸውንም ሳይሆን ጀርባቸውን ሰጡኝ፥ በመከራቸው ጊዜ ግን፦ ‘ተነሥተህ አድነን’ ይላሉ።


በውኑ የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስና ሕዝቡ ሁሉ ገደሉትን? በውኑ ንጉሡ ጌታን አልፈራን? ወደ ጌታስ አልተማጠነምን? ጌታስ በእነርሱ ላይ የተናገረውን ክፉ ነገር አልተወምን? እኛም በነፍሳችን ላይ ታላቅ ክፋት እናደርጋለን።”


“እናንተና አባቶቻችሁ ነገሥታቶቻችሁም አለቆቻችሁም የምድሪቱም ሕዝብ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባይ ያጠናችሁትን ዕጣን ጌታ አያስታውሰውምን? በልቡስ አያኖረውምን?


አባቶቻችን ኃጢአትን ሠሩ ዛሬም የሉም፥ እኛም በደላቸውን ተሸከምን።


እነሆም ልጅ ቢወልድ፥ እርሱም አባቱ የሠራውን ኃጢአት ቢያይ፥ ቢፈራ፥ እነዚህንም ባይሠራ፥


ወደ ጌታ ቤት ወደ ውስጠኛው አደባባይ አመጣኝ፥ እነሆ በጌታ መቅደስ መግቢያ፥ በመተላለፊያውና በመሠዊያው መካከል ሃያ አምስት ያህል ሰዎች ነበሩ፥ ጀርባቸው ወደ ጌታ መቅደስ ፊታቸውም ወደ ምሥራቅ ነበረ፥ እነርሱም ወደ ምሥራቅ ለፀሐይ ይሰግዱ ነበር።


ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔም ይልቅ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos