2 ዜና መዋዕል 25:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)27 አሜስያስም ጌታን ከመከተል ከራቀ በኋላ በኢየሩሳሌም ሤራን አሤሩበት፥ ወደ ለኪሶም ኰበለለ፤ ከኋላውም የሚከታተሉትን ሰዎች ወደ ለኪሶ ላኩበት፥ በዚያም ገደሉት። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም27 አሜስያስ እግዚአብሔርን መከተል ከተወ በኋላ፣ አሜስያስ በኢየሩሳሌም ሤራ ስለ ጠነሰሱበት ሸሽቶ ወደ ለኪሶ ሄደ፤ እነርሱ ግን የሚከታተሉትን ሰዎች ወደ ለኪሶ ላኩ፤ እነርሱም ገደሉት። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም27 አሜስያስ እግዚአብሔርን ከተወበት ጊዜ ጀምሮ በኢየሩሳሌም ውስጥ እርሱን ለመግደል ሤራ ተጠንስሶ ነበር፤ በመጨረሻም አሜስያስ ሸሽቶ ወደ ላኪሽ ሄደ፤ ነገር ግን ጠላቶቹ እዚያው ድረስ ልከው አስገደሉት፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)27 አሜስያስም እግዚአብሔርን ከመከተል በራቀ ጊዜ በኢየሩሳሌም የዐመፅ መሐላ አደረጉበት፤ ወደ ለኪሶም ኮበለለ፤ በስተኋላውም ወደ ለኪሶ ላኩ፤ በዚያም ገደሉት። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)27 አሜስያስም እግዚአብሔርን ከመከተል ከራቀ በኋላ በኢየሩሳሌም የዓመፅ መሐላ አደረጉበት፤ ወደ ለኪሶም ኵበለለ፤ በስተ ኋላውም ወደ ለኪሶ ላኩ፤ በዚያም ገደሉት። Ver Capítulo |