Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 24:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ወደ ጌታም እንዲመልሱአቸው ነቢያትን ይልክላቸው ነበር፤ መሰከሩባቸውም፥ እነርሱ ግን አላደመጡም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ወደ እግዚአብሔር ይመልሷቸው ዘንድ እርሱ ነቢያቱን ወደ ሕዝቡ ሰደደ፤ ነቢያቱም መሰከሩባቸው፤ እነርሱ ግን አላዳመጡም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እግዚአብሔር ወደ እርሱ እንዲመለሱ አጥብቀው ያሳስቡአቸው ዘንድ ነቢያትን ላከ፤ መሰከሩባቸውም፤ እነርሱ ግን አላዳመጡም፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይመ​ል​ሱ​አ​ቸው ዘንድ ነቢ​ያ​ትን ይሰ​ድ​ድ​ላ​ቸው ነበር፤ መሰ​ከ​ሩ​ባ​ቸ​ውም፤ እነ​ርሱ ግን አላ​ደ​መ​ጡም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ወደ እግዚአብሔርም ይመልሱአቸው ዘንድ ነቢያትን ይሰድድላቸው ነበር፤ መሰከሩባቸውም፤ እነርሱ ግን አላደመጡም።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 24:19
23 Referencias Cruzadas  

ደግሞም በጌታ አምሎት በነበረው በንጉሡ በናቡከደናፆር ላይ ዓመፀ፤ ወደ እስራኤልም አምላክ ወደ ጌታ እንዳይመለስ አንገቱን አደነደነ ልቡንም አጠነከረ።


“ነገር ግን እንቢተኞች ነበሩ፥ ዐመፁብህም፥ ሕግህንም ወደ ኋላቸው ጣሉት፥ ወደ አንተም ይመለሱ ዘንድ የመሰከሩባቸውን ነቢያትህን ገደሉ፥ እጅግም አስቆጡህ።


ነገር ግን ብዙ ዓመታት ታገሥሃቸው፥ በነቢያትህም እጅ በመንፈስህ መሰከርክባቸው፥ አላደመጡም፥ ስለዚህም በምድር አሕዛብ እጅ አሳልፈህ ሰጠሃቸው።


አድምጡ ድምፄንም ስሙ፤ ልብ አድርጉ ንግግሬንም ስሙ።


ከመካከላችሁ ይህን የሚያደምጥ፥ ለሚመጣውም ጊዜ የሚያደምጥና የሚሰማ ማን ነው?


ወገኔ ሆይ፥ አድምጠኝ፤ ሕዝቤ ሆይ፥ ስማኝ፤ ሕግ ከእኔ ይወጣልና ፍርዴም ለአሕዛብ ብርሃን ይሆናልና።


ጆሮአችሁን አዘንብሉ ወደ እኔም ቅረቡ፤ ሰውነታችሁ በሕይወት እንድትኖር ስሙኝ፥ የታመነችይቱን የዳዊትን ምሕረት፥ የዘለዓለምን ቃል ኪዳን ከእናንተ ጋር አደርጋለሁ።


ከይሁዳ ንጉሥ ከአሞጽ ልጅ ከኢዮስያስ ከዐሥራ ሦስተኛው ዓመት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ባሉት በእነዚህ በሀያ ሦስቱ ዓመታት፥ የጌታ ቃል ወደ እኔ መጣ፥ እኔም ማልጄ ተነሥቼ ተናገርኋችሁ፤ ተናገርሁ፥ ሆኖም ግን አልሰማችሁም።


ለእናንተ ጉዳት እንዲሆን በእጃችሁ ሥራ አስቆጣችሁኝ እንጂ አልሰማችሁኝም፥ ይላል ጌታ።


ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ቃሎቼን አልሰማችሁምና


ያልሰማችሁትን በማለዳ ተነሥቼ ወደ እናንተ የላክኋቸውን የባርያዎቼን የነቢያትን ቃላት ባትሰሙ፥


የቀደሙት ነቢያት ለአባቶቻችሁ እንዲህ ብለው ሰብከዋል፦ “የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱ፤’” እነርሱ ግን አልሰሙም፤ እኔንም አላደመጡም፤ እንደ እነርሱ አትሁኑ፥ ይላል ጌታ።


የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።”


‘ሙሴንና ነቢያትንም የማይሰሙ ከሆነ፥ ከሙታንም እንኳ አንድ ሰው ቢነሣ አያምኑም፤’ አለው።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos