Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 2:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 እኛም ከሊባኖስ የምትሻውን ያህል እንጨት እንቈርጣለን፥ በታንኳም አድርገን በባሕር ላይ ወደ አንተ ወደ ኢዮጴ እናመጣለን፤ አንተም ወደ ኢየሩሳሌም ታስወስደዋለህ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እኛም የሚያስፈልግህን ግንድ ሁሉ ከሊባኖስ ቈርጠንና አስረን እስከ ኢዮጴ ድረስ ቍልቍል በማንሳፈፍ እንሰድድልሃለን፤ አንተም ወደ ኢየሩሳሌም ታስወስደዋለህ።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እኛም የምትፈልገውን ግንድ ሁሉ ከሊባኖስ ተራራዎች ቈርጠን አንድ ላይ በማሰር በባሕር ላይ ተንሳፍፎ እስከ ኢዮጴ እንዲደርስ እናደርጋለን፤ ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ልትወስደው ትችላለህ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እኛም ከሊ​ባ​ኖስ የም​ት​ሻ​ውን ያህል እን​ጨት እን​ቈ​ር​ጣ​ለን፤ በታ​ን​ኳም አድ​ር​ገን በባ​ሕር ላይ ወደ አንተ ወደ ኢዮጴ እን​ል​ካ​ለን፤ አን​ተም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ታስ​ወ​ስ​ደ​ዋ​ለህ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እኛም ከሊባኖስ የምትሻውን ያህል እንጨት እንቈርጣለን፤ በታንኳም አድርገን በባሕር ላይ ወደ አንተ ወደ ኢዮጴ እንሰድዳለን፤ አንተም ወደ ኢየሩሳሌም ታስወስደዋለህ።”

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 2:16
15 Referencias Cruzadas  

ዳዊትም በእስራኤል ምድር የነበሩትን መጻተኞች እንዲሰበስቡ አዘዘ፤ የእግዚአብሔርንም ቤት ለመሥራት የሚወቀሩትን ድንጋዮች እንዲወቅሩ ጠራቢዎችን አኖረ።


የይሁዳም ጉባኤ ሁሉ፥ ካህናቱና ሌዋውያኑ፥ ከእስራኤልም የመጡ ጉባኤ ሁሉ፥ ከእስራኤልም አገር የመጡትና በይሁዳ የኖሩት እንግዶች ደስ አላቸው።


ከኬጢያውያንም ከአሞራውያንም ከፌርዜያውያንም ከኤዊያውያንም ከኢያቡሳውያንም የቀሩትን ከእስራኤል ወገን ያልሆኑትን ሕዝብ ሁሉ፥


የእስራኤልም ልጆች ያላጠፉአቸውን፥ በኋላቸው በምድሪቱ ላይ የቀሩትን ልጆቻቸውን ሰሎሞን እስከ ዛሬ ድረስ ገባሮች አድርጎ መለመላቸው።


ለጠራቢዎችና ለአናጢዎችም ገንዘብ ሰጡ፤ የፋርስም ንጉሥ ቂሮስ እንደ ፈቀደላቸው የዝግባ ዛፍ ከሊባኖስ ወደ ያፎ ባሕር እንዲያመጡ ለሲዶናውያንና ለጢሮሳውያን መብልና መጠጥ ዘይትም ሰጡ።


ዮናስ ግን ከጌታ ፊት ወደ ተርሴስ ለመሸሽ ተነሣ፤ ወደ ያፎም ወረደ፥ ወደ ተርሴስም የምትሄድ መርከብ አገኘ፤ ከጌታ ፊት ሸሽቶ ከእነርሱ ጋር ወደ ተርሴስ ለመሄድ ዋጋ ሰጥቶ ወደ እርሷ ገባ።


ሁሉ በእርሱ ሆነ፤ ከሆነውም ሁሉ አንድም ነገር ያለ እርሱ የሆነ የለም።


እንግዲህ ወደ ኢዮጴ ልከህ ጴጥሮስ የተባለውን ስምዖንን አስጠራ፤ እርሱ በቁርበት ፋቂው በስምዖን ቤት በባሕር አጠገብ በእንግድነት ተቀምጦአል፤’ አለኝ።


በኢዮጴም ጣቢታ የሚሉአት አንዲት ደቀመዝሙር ነበረች፤ ትርጓሜውም ዶርቃ ማለት ነው፤ እርሷም መልካም ነገር የሞላባት ምጽዋትም የምታደርግ ነበረች።


ልዳም ለኢዮጴ ቅርብ ናትና ደቀ መዛሙርት ጴጥሮስ በዚያ እንዳለ ሰምተው፥ ወደ እነርሱ ከመምጣት እንዳይዘገይ እየለመኑ ሁለት ሰዎች ወደ እርሱ ላኩ።


ይህም በኢዮጴ ሁሉ የታወቀ ሆነ፤ ብዙ ሰዎችም በጌታ አመኑ።


በኢዮጴም ስምዖን ከሚሉት ከአንድ ቁርበት ፋቂ ጋር አያሌ ቀን ኖረ።


ሜያ-ርቆንን፥ በኢዮጴ ፊት ለፊት ካለው ዳርቻ ጋር ራቆንን ነበር።


በዚያም ቀን ኢያሱ በመረጠው ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ ለማኅበሩና ለጌታ መሠዊያ እንጨት ቈራጮች ውኃም ቀጂዎች አደረጋቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos