Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 18:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 አንድ ሰውም ቀስቱን በድንገት ገትሮ የእስራኤልን ንጉሥ በጥሩሩ መጋጠሚያ በኩል ሳንባውን ወጋው። ሰረጋለኛውንም፦ “ተወግቻለሁና ሠረገላውን አዙር ከጦርነቱም ውስጥ አውጣኝ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ይሁን እንጂ አንዱ ቀስቱን በነሲብ ቢያስፈነጥረው፣ በጥሩሩ መጋጠሚያዎች መካከል ዐልፎ የእስራኤልን ንጉሥ ወጋው። ንጉሡም ሠረገላ ነጂውን “ተመለስና ከጦርነቱ አውጣኝ፤ ቈስያለሁና” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ይሁን እንጂ አንድ የሶርያ ወታደር በአጋጣሚ ያስፈነጠረው ፍላጻ በጥሩሩ መጋጠሚያ በኩል አልፎ አክዓብን መታው፤ ንጉሥ አክዓብም የሠረገላ ነጂውን “እኔ ቈስያለሁ! ስለዚህ ሠረገላውን መልሰህ ከጦር ሜዳው ውጣ!” ሲል አዘዘው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 አንድ ሰውም ቀስ​ቱን በድ​ን​ገት ገትሮ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ በጥ​ሩሩ መጋ​ጠ​ሚያ በኩል ሳን​ባ​ውን ወጋው። ሰረ​ገ​ለ​ኛ​ው​ንም፥ “ተወ​ግ​ቻ​ለ​ሁና እጅ​ህን ግታ፤ ከጦ​ር​ነት ውስጥ አው​ጣኝ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 አንድ ሰውም ቀስቱን በድንገት ገትሮ የእስራኤልን ንጉሥ በጥሩሩ መጋጠሚያ በኩል ሳንባውን ወጋው። ሰረጋለኛውንም “ተወግቻለሁና እጅህን ግታ፤ ከሰልፍም ውስጥ አውጣኝ” አለው።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 18:33
5 Referencias Cruzadas  

ከአቤሴሎም ጋር ከኢየሩሳሌምም ሁለት መቶ ሰዎች አብረውት ሄደው ነበር፤ በእንግድነት ተጋብዘው በቅንነት ከመሄዳቸው በስተቀር፥ ስለጉዳዩ ምንም ነገር አያውቁም ነበር።


የሰረገሎቹም አለቆች የእስራኤል ንጉሥ እንዳልሆነ ባዩ ጊዜ እርሱን ከማሳደድ ተመለሱ።


በዚያም ቀን ጦርነቱ በረታ፤ የእስራኤልም ንጉሥ በሶርያውያን ፊት እስከ ማታ ድረስ በሠረገላው ላይ ራሱን አስደግፎ ተንጋለለ፤ ፀሐይም በጠለቀች ጊዜ ሞተ።


ቀስተኞችም ንጉሡን ኢዮስያስን ወጉት፤ ንጉሡም አገልጋዮቹን፦ “ክፉኛ ቆስያለሁና ከሰልፉ ውስጥ አውጡኝ” አላቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos