Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 13:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ኢዮርብዓም ግን ድብቅ ጦር በስተ ኋላቸው አዞረ፤ እነርሱ በይሁዳ ፊት ለፊት ሆነው ድብቅ ጦሩ ግን በስተ ኋላቸው ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 በዚህ ጊዜ ኢዮርብዓም ከሰራዊቱ ከፊሉን ከይሁዳ ሰራዊት በስተጀርባ እንዲያደፍጡ ላከ፤ የቀረውም ሰራዊት ከርሱ ጋራ የይሁዳን ሰራዊት ፊት ለፊት እንዲገጥሙ አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 በዚህ ጊዜ ኢዮርብዓም ከሠራዊቱ ከፊሉን ከይሁዳ ሠራዊት በስተጀርባ በማድፈጥ፥ አደጋ እንዲጥሉ ሲልክ፥ የቀሩትን ደግሞ የይሁዳን ሠራዊት ፊት ለፊት እንዲገጥሙአቸው አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ኢዮ​ር​ብ​ዓም ግን በስ​ተ​ኋ​ላ​ቸው ይመ​ጣ​ባ​ቸው ዘንድ ድብቅ ጦር አዞ​ረ​ባ​ቸው፤ እነ​ርሱ በይ​ሁዳ ሰፈር ፊት ሳሉ ድብቅ ጦሩ በስ​ተ​ኋ​ላ​ቸው ከበ​ባ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ኢዮርብዓም ግን ድብቅ ጦር በስተኋላቸው አዞረ፤ እነርሱ በይሁዳ ፊት ሆነው ድብቅ ጦሩ በስተ ኋላቸው ነበረ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 13:13
6 Referencias Cruzadas  

ኢያሱም ሰደዳቸው፤ ወደሚደበቁበትም ስፍራ ሄዱ፥ በጋይና በቤቴል መካከልም በጋይ በምዕራብ በኩል ተቀመጡ፤ ኢያሱ ግን በዚያች ሌሊት በሕዝቡ መካከል አደረ።


እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፦ “እነሆ፥ ከከተማይቱ በስተ ኋላ ተደበቁ፤ ከከተማይቱ አትራቁ፥ ሁላችሁም ነቅታችሁ ጠብቁ፤


“ሕዝቤ ሰንፈዋልና አላወቁኝም፤ ሰነፎች ልጆች ናቸው፥ ማስተዋልም የላቸውም፤ ክፉ ነገርን ለማድረግ ብልሃተኞች ናቸው፥ በጎ ነገርን ማድረግ ግን አያውቁም።”


ያለ ጌታ የሚሠምር፥ ጥበብም የለም፥ ማስተዋልም የለም፥ ምክርም የለም።


ዝማሬውንና ምስጋናውንም በጀመሩ ጊዜ ይሁዳን ሊወጉ በመጡ በአሞንና በሙዓብ ልጆች በሴይርም ተራራ ሰዎች ላይ ጌታ ድብቅ ጦርን አመጣባቸው፤ እነርሱም ተሸነፉ።


ኢዮርብዓም በእስራኤል ላይ በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት አቢያ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios