Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 10:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 “አባትህ ቀንበር አክብዶብን ነበር፤ ስለዚህ አሁን አንተ ጽኑውን የአባትህን አገዛዝ፥ በላያችንም የጫነውን የከበደውን ቀንበር አቅልልልን፥ እኛም እናገለግልሃለን።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 “አባትህ ቀንበራችንን አከበደብን፤ አንተ ግን አስጨናቂውን ሥራና በላያችን የጫነብንን ከባድ ቀንበር አቅልልልን፤ እኛም እንገዛልሃለን።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 “አባትህ ሰሎሞን በእኛ ላይ ከባድ የአገዛዝ ቀንበር ጭኖ አስጨንቆን ነበር፤ ከችግራችን ብታወጣን እንገዛልሃለን” አሉት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 “አባ​ትህ ቀን​በር አክ​ብ​ዶ​ብን ነበር፤ አሁ​ንም አንተ ጽኑ​ውን የአ​ባ​ት​ህን አገ​ዛዝ፥ በላ​ያ​ች​ንም የጫ​ነ​ውን የከ​በ​ደ​ውን ቀን​በር አቅ​ል​ል​ልን፥ እኛም እን​ገ​ዛ​ል​ሃ​ለን።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 “አባትህ ቀንበር አክብዶብን ነበር፤ አሁንም አንተ ጽኑውን የአባትህን አገዛዝ፥ በላያችንም የጫነውን የከበደውን ቀንበር አቅልልልን፤ እኛም እንገዛልሃለን፤” ብለው ተናገሩት።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 10:4
15 Referencias Cruzadas  

“አባትህ ሰሎሞን በእኛ ላይ ከባድ የአገዛዝ ቀንበር ጭኖ አስጨንቆን ነበር፤ አሁን ይህን ከባድ ሸክም ብታቃልልልንና ኑሮአችንን ብታሻሽልልን እኛ ለአንተ እንገዛልሃለን” አሉት።


የይሁዳና የእስራኤል ሕዝብ ብዛት እንደ ባሕር ዳር አሸዋ ነበር፤ እነዚህ ሁሉ እየበሉና እየጠጡ ዘወትር ደስ ይሰኙ ነበር።


በኖረበትም ዘመን ሁሉ ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ መላው የይሁዳና የእስራኤል ሕዝብ ያለ ስጋት በሰላም ይኖር ነበር፤ እያንዳንዱም ቤተሰብ የራሱ የሆነ የወይን ተክልና የበለስ ዛፍ ስለ ነበረው በእነዚህ ተክሎች ጥላ ሥር ያርፍ ነበር።


ንጉሥ ሰሎሞን ከመላው እስራኤል ሠላሳ ሺህ የግዳጅ ሠራተኞችን መለመለ።


ንጉሥ ሰሎሞን በኮረብታማው አገር ድንጋይ የሚፈልጡ ሰማኒያ ሺህ፥ የተፈለጠውን ድንጋይ ተሸክመው የሚያመጡ ሰባ ሺህ ሰዎችን መደበ።


ሰሎሞን ከእስራኤላውያን ወገን ማንንም ባርያ አድርጎ አላሠራም፤ እነርሱ ባለ ሥልጣኖች፥ ወታደሮች፥ የጦር መኰንኖች፥ የጦር አዛዦች፥ ሠረገላ ለሚነዱ ሁሉ ኀላፊዎችና ፈረሰኞች ሆነው ያገለግሉ ነበር።


ልከውም ጠሩት፤ ኢዮርብዓምና እስራኤልም ሁሉ መጥተው ሮብዓምን እንዲህ አሉት፦


እርሱም፦ “ከሦስት ቀን በኋላ ወደ እኔ ተመለሱ” አላቸው። ሕዝቡም ሄዱ።


ከብዙ ቀኖች በኋላ የግብጽ ንጉሥ ሞተ፤ የእስራኤልም ሕዝቦች ከባርነት የተነሣ አለቀሱ፥ ጮኹም፥ ስለባርነታቸውም የልመና ጩኸታቸው ወደ እግዚአብሔር ወጣ።


በሕዝቤ ላይ ተቈጥቼ ነበር፤ ርስቴንም አረከስሁ፤ በእጅሽም አሳልፌ ሰጠኋቸው፤ ከእነርሱ ጋር ምሕረት አላደረግሽም፤ በሽማግሌዎቻቸው ላይ ቀንበርሽን እጅግ አክብደሻል።


ከባድና አስቸጋሪ ሸክም አስረው በሰው ትከሻ ላይ ይጭናሉ፤ እነርሱ ግን በጣታቸው እንኳ ሊነኩት አይፈልጉም።


ትእዛዛቱን እንድንጠብቅ፥ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና፤ ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos