1 ተሰሎንቄ 2:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 እኛ ግን ወንድሞች ሆይ! በልብ ሳይሆን በአካል ለጥቂት ጊዜ ብናጣችሁም፥ በብዙ ናፍቆት ግን ፊታችሁን ለማየት እጅግ ጓጓን፤ Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 ነገር ግን ወንድሞች ሆይ፤ እኛ በልባችን ሳይሆን በአካል ለጥቂት ጊዜ ከእናንተ ብንለይም፣ ለእናንተ ካለን ታላቅ ናፍቆት የተነሣ ፊታችሁን ለማየት ብርቱ ጥረት አደረግን። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 ነገር ግን ወንድሞች ሆይ! በመንፈስ ሳይሆን በሥጋ ለጥቂት ጊዜ ከእናንተ በመለየታችን ስለ እናንተ ያለን ናፍቆት ብዙ ስለ ሆነ በዐይነ ሥጋ ልናያችሁ ብዙ ጥረት አደረግን። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 እኛ ግን ወንድሞች ሆይ! በልብ ያይደለ ፊት ለፊት ለጥቂት ጊዜ አጥተናችሁ፥ በብዙ ናፍቆት ፊታችሁን ለማየት እጅግ ሞከርን፤ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 እኛ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ በልብ ያይደለ ፊት ለፊት ለጥቂት ጊዜ አጥተናችሁ፥ በብዙ ናፍቆት ፊታችሁን ለማየት እጅግ ሞከርን፤ Ver Capítulo |