Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ተሰሎንቄ 1:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በእግዚአብሔር የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ! በእርሱ መመረጣችሁን አውቀናል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በእግዚአብሔር የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ፣ እርሱ እንደ መረጣችሁ እናውቃለን፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በእግዚአብሔር የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ፥ እግዚአብሔር እንደ መረጣችሁ እናውቃለን።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በእግዚአብሔር የምትወደዱ ወንድሞች ሆይ! እንደ ተመረጣችሁ አውቀናልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በእግዚአብሔር የምትወደዱ ወንድሞች ሆይ፥ እንደ ተመረጣችሁ አውቀናልና።

Ver Capítulo Copiar




1 ተሰሎንቄ 1:4
14 Referencias Cruzadas  

በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ! እኛ ግን ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ሁልጊዜ ልናመሰግን ይገባናል፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ከመጀመሪያው አንሥቶ በመንፈስ በመቀደስና በእውነት በማመን እንድትድኑ መርጦአችኋልና፤


ስለዚህ ወንድሞች ሆይ! መጠራታችሁንና መመረጣችሁን እንድታጸኑ፥ ከፊት ይልቅ ትጉ፤ ይህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉም።


በሆሴዕ ደግሞ እንዲህ እንደሚል፤ “ሕዝቤ ያልሆነውን ‘ሕዝቤ’ ብዬ፥ ያልተወደደችውንም ‘የተወደደችው’ ብዬ እጠራለሁ፤


እንግዲህ እንደ እግዚአብሔር ምርጦች ቅዱሳንና የተወደዳችሁ ሆናችሁ፥ ምሕረትን፥ ርኅራኄን፥ ቸርነትን፥ ትሕትናን፥ የዋህነትን፥ ትዕግሥትን ልበሱ፤


ዓለም ሳይፈጠር፥ በፍቅር በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን እድንሆን በክርስቶስ መረጠን።


በእግዚአብሔር ለተወደዳችሁ፥ በሮሜ ላላችሁ ሁሉ፥ ቅዱሳን ልትሆኑ ለተጠራችሁ ከአባታችን ከእግዚአብሔር ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።


እግዚአብሔር አብ አስቀድሞ ያወቃችሁ፥ በመንፈስ የተቀደሳቹ፥ ለኢየሱስ ክርስቶስ ትታዘዙና በደሙም ትረጩ ዘንድ ለተመረጣችሁት፥ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።


በእግዚአብሔር በአባታችን ፊት የእምነታችሁን ሥራ፥ የፍቅራችሁን ድካም፥ በጌታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ያላችሁን የተስፋችሁንም መጽናት እናስታውሳለን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios