1 ሳሙኤል 31:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ከዚያም የሳኦልን ራስ ቆርጠው፥ የጦር መሣሪያውንም ገፈው፥ የምሥራቹን በየቤተ ጣዖቶቻቸውና በሕዝባቸው መካከል እንዲናገሩ ወደ ፍልስጥኤም ምድር ሁሉ መልክተኞች ላኩ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ከዚያም የሳኦልን ራስ ቈርጠው፣ የጦር መሣሪያውንም ገፍፈው፣ ለቤተ ጣዖቶቻቸውና ለሕዝቡ የምሥራቹን እንዲናገሩ ወደ መላው የፍልስጥኤም ምድር መልክተኞችን ላኩ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 የሳኦልንም ራስ ቈርጠው የጦር ልብሱንም ገፈው በማስያዝ ለአማልክቶቻቸው መቅደስና ለሕዝባቸው የድሉን ዜና ያበሥሩ ዘንድ መልእክተኞቻቸውን ላኩ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 አገላብጠውም የጦር መሣሪያዎችን ገፈፉ፤ በዙሪያቸውም ላሉ ለጣዖታቱና ለሕዝቡ የምሥራች ይነግሩ ዘንድ ወደ ፍልስጥኤማውያን ሀገር ሁሉ ላኩ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 የሳኦልንም ራስ ቈርጠው የጦር ዕቃውን ገፍፈው ለጣዖታቱ መቅደስ ለሕዝቡም የምስራች ይሰጥ ዘንድ ወደ ፍልስጥኤማውያን አገር ሁሉ ሰደዱ። Ver Capítulo |